የሥነ ጽሑፍ ዋርካው ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው የቀብር ስነስርዓት ተፈፅመ

የስነፁሑፋ ዋርካው ዘሪሁን አስፉው የቀብር ስነስርዓት ረብዕ የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በክብር ተፈፅሟል:: በዚሁ የቀብር ስነስርዓት ላይ የመንግስት የስራ ሐላፊዎች ምሁራን ወዳጅ ዘመዶቻቸው የስራ ባልደረቦቻቸው የስነፁሑፍ ባለሙያዎች ደራሲያን ጋዜጠኛች የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት በታላቅ ክብር በቅድስት ስላሴ ካቴድራል የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈፅሟል::
የአቶ ዘሪሁን አስፋው አጭር የህይወት ታሪክ
ዘሪሁን አስፋው ከአባታቸው ከአቶ አስፋው ጎበናና ከእናታቸው ከወ/ሮ ስህን ጎበና ጥቅምት 10 ቀን 1944 ዓ.ም በደሴ ከተማ ተወለዱ:: ዘሪሁን አስፋው የመጀመሪያ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በደሴ አካለወልድ ት/ቤት እና በወይዘሮ ስህን ት/ቤት ተማረ:: በወይዘሮ ስህን ት/ቤት ከመደበኛ ትምህርቱ በተጨማሪ የትምህርት ቤቱ የኪነጥበብ አባል ሆኖ በቲያትር ትወና በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት በመሳተፍ በኃለኛው ዘመን እድሜውን ሙሉ ለዋኝበት የስነፁሑፍ ህይወቱ እንዳደላደለበት የሚታወቅ ነው::በ1962 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በልዑል በዕደማርያም የመሰናዶ ት/ቤት መማር ከጀመረ በኃላ የጥበብ ጥሪውን ተከትሎ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩንቨርስቲ የባህል ማዕከል አባል በመሆን በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ የነበረውን ኪነጥበባዊ ተግባሩን ገፍቶበታል::በመቀጠልም በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍለ ትምህርት ከ1963 ዓ.ም እስከ 1965 ዓ.ም የሶስት ዓመት የዩንቨርስቲ ትምህርት ካጠናቀቀ በኃላ በወቅቱ አስፈላጊ በነበረው የዩንቨርስቲ አገልግሎት በመሳተፍ በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት በከረን ከተማ ለአንድ አመት ያህል አስተምሮና ግዳጁን ተውጥቶ ተመልሷል:: ከዚያም በኃላ በ1967 ዓ.ም በታወጀው የእድገት በህብረት የዕውቀትና የስራ ዘመቻ ተሳታፊ በመሆን በትግራይ ጠቅላይ ግዛት በዓደዋና አካባቢው ተመድቦ ግዳጁን ተወጥቷል::በዩንቨርሲቲ አገልግሎትና በእድገት በህብረት ዘመቻ ምክንያት ለሶስት ዓመታት ያቋረጠውን ትምህርት ለመቀጠል ቢሞክርም በወቅቱ በነበረው በልዩ ልዩ የፓለቲካ ኃይሎች ትርምስ በቀይና ነጭ ሽብር ምክንያት ተረጋግቶ መማር ባለመቻሉ ወደ አሩሲ ክ/ሃገር አሰላ ከተማ በመሄድ አሰላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አማርኛና እንግሊዘኛ ትምህርት እያስተማረ ለአንድ አመት አስተምሮ ተመለሰ::ከዚያም ተመልሶ ያቋረጠውን ትምህርት በመቀጠል በሚገባ አጠናቆ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍለ ትምህርት በ1970 ዓ.ም የመጀምሪያ ዲግሪውን አገኝ:: የሁለተኛ ዲግሪውንም ከዚሁ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የውጪ ቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍለ ትምህርት ከ1973-1975 ዓ.ም ተከታትሎ በስነፁሑ የማስተርስ ዲግሪውን ተቀበለ::
ስራ
===
አቶ ዘሪሁን አስፋው በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ቋንቋዎችና ስነፁሑፍ ክፍለ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪውን ካገኝ በኃላ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስር በነበረው የአለማያ ግብርና ኮሌጅ በረዳት ምሩቅነት ደረጃ በ1971 ዓ.ም ተቀጥሮ እስከ ሌክቸረርነት ደረጃ በማደግ እስከ 1975 ዓ.ም ድረስ በመምህርነትና በተከታታይ ትምህርት አስተባባሪነት አገልግሏል::ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ድረስ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋና ፎክሎር ስነፁሑፍ ክፍለ ትምህርት ውስጥ በተለያዩ ማዕረጎችና ኃላፊነቶች አገልግሏል::ይህም ማለት ከ1976 -1986 ዓ.ም በሌክቸረርነት ከ1986- 1993 ዓ.ም በረዳት ፕሮፌሰርነት ከ1993 ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ድረስ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት ሲያገለግል ቆይቷአል:: አቶ ዘሪሁን አስፋው በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ላለፉት 40 ዓመታት ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ድረስ በርካታ ተማሪዎችን ሲያስተምር ቆይቷል:: በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ውስጥ ከማስተማር ጎን ለጎን 143 የመጀመሪያ ዲግሪ 80 የማስተርስ ዲግሪ 20 የዶክቶሬት ዲግሪ ተማሪዎችን በምርምር ስራዎቻቸው አማክሯል::
ዘሪሁን አስፋው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ40 ዓመት በላይ በሥነጽሑፍ መምህርነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በተለያዩ ሥነ ጽሑፋዊ ጉዳዮች ላይ ጥናትና እና ምርምሮችን አካሂደዋል::አቶ ዘሪሁን አስፋው ከትምህርቱ ዘርፍ በተጨማሪ ከፖፑሌየሽን ሚዲያ ሴንተር ጋር በመሆን የተለያዩ የሥነ ሕዝብ ጥናቶችን የሰሩ ሲሆን፣ ወጣት ደራሲያን እና ተመራማሪዎችን በማማከር እና በመደገፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል:: ተ/ፕሮፌሰር ዘሪሁን በማስተማር ሥራቸው ብቻ ሳይሆን በጥናት እና ምርምር ሥራዎች ላይ”የኢትዮጵያን ሥነጽሑፍ ታላላቅ የስነፁሑፍ ስራዎችን የሰነዱ” ታላቅ መምህር ነበሩ::
ዘሪሁን አስፋው ከምርምር ስራዎቻቸው በተጨማሪ አምስት መፅሐፍትን አሳትመዋል:: እነዚህም 1.የሥነጽሁፍ መሠረታውያን 2.ልቦለዳዊያንና የቀደምት ደራስያን አጫጭር ትረካዎች 3.ስነፁሑፍ ለማህበራዊ ለውጥ ( ከፓፕሌሽን ሚዲያ ጋር) 4. ከበዓሉ ግርማ እስከ አዳም ረታ 5. በስነጽሑፍና በፎክሎር የተሰሩ የዲግሪ ማሙያ ጥናቶችና አጠቃሎ ስብስብ የሚሉት ቀዳሚዎቹ ናቸው::ከእነዚህ ስራወች በተጨማሪ እጅግ በርካታ የምርምርና የጥናት ስራወችን በታወቁ የጥናት መፅሔቶችና ታላላቅ ጉባዔዎች ላይ ታትመውለታል:: በርካታ ያልታተሙ በርካታ ስራዎችም አሉት:: ዘሪሁን አስፋው በሐገር ውስጥ ካበረከታቸው ተሳትፎ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ መድረኮችም ተሳትፎ ነበረ:: ከእነዚህ መካከልም በአሜሪካ በጃፓንደቡብ አፍሪካ ዛምቢያደቡብ ኮሪያ እንግሊዝና ጀርመን የሚገኙ ቀዳሚ ተጠቃሽ ናቸው::
አቶ ዘሪሁን አስፋው ገና በጠዋቱ በትምህርት ቤት የኪነጥበብ ክበብ የጀመረውን ንቁ ተሳታፊነት ቀስ በቀስ እያሳደገና እያጠናከረ የህይወቱ ድርና ማግ ያደረገ በጥልቅ ተመልካችነት ስነፁሁፍን የተጠበበ የመረመረ የሄሰ የሐገራችንን አንጋፋና ወጣት ተመራማሪዎችንም ሆነ ፈጣሪዎች በረቂቁ የአስተሳሰብ መንገድና የአሰራር ብልሃታቸው ያስገኙትን ትሩፋት አንጥሮ በማሳየት ዘወትር የሚተጋ ነበረ:: በአጠቃላይ አቶ ዘሪሁን አስፋው ለኢትዮጵያ ስነፁሑፍ እድገትም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ታላቅ ምሁር ነበሩ:: ዘሪሁን አስፋውበተወለዱ በ71 ዓመታቸውየካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ምከዚህ ዓለም ድካም ተገላግለዋል::
ዘሪሁን አስፋው 40 ዓመት በትዳር ከቆዩት ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የትምወርቅ አካሉ ሶስት ወንድና አንድ ሴት ልጆች ያፈሩ ሲሆን ይሁንና አንዱ ወንድ ልጃቸው ከአመት በፊት በህይወት ተለይቷል:: እግዚአብሔር ነፍሱን ይማር!!
(ይትባረክ ዋለልኝ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe