የሩሲያ መከላከያ 555 የዩክሬን ድሮኖችን በአንድ ሌሊት ብቻ መትቶ መጣሉን ይፋ አደረገ

ዩክሬን የሞስኮን የነዳጅ መጣሪያ መታች፡፡ ዩክሬን ይህን ጥቃት በሩሲያ ላይ የፈጸመችው ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ትራምፕ ጦርነቱን ለመቋጨት ድጋፍ እየጠየቁ ባለበት ወቅት ነው፡፡

የዩክሬን ድሮኖች የሞስኮን ነዳጅ ማጣሪያን በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁተኛ ጊዜ መምታታቸው ሲነገር፤ሩሲያም ሚሳኤሎችን በማስወንጨፍ በኪቭ ላይ ጥቃት ፈጽማለች፡፡

ጦርነቱ በተለያዩ ጥቃቶች ታጅቦ በቀጠለበት በዚህ ስዓት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አሜሪካ እና አውሮፓ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ከስምምነት ላይ እንድትደርስ እንዲያግዟት ጠይቀዋል፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ሃሙስ እንዳለው በትላንት ምሽት ብቻ 555 የዩክሬን ድሮኖች ተመጠው ተጥለዋል በተጨማሪም ወደ 200 የሚደርሱት ደግሞ ከሞስኮ በቅርብ ርቀት መቀልበስ እንደተቻለም ገልጻል፡፡

ይህ የአሁኑ የአየር ጥቃት የማክሰኞውን ጨምሮ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው፡፡ በተመሳሳይ የዩክሬኗ ኪቭም በሩሲያ ባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ስተናጥ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ ሮይተርስ ጽፏል፡፡

የዩክሬን ባለስልጣናት ጠላታችን ሩሲያ ዋና ከተማችንን በባላስቲክ ሚሳኤል አጥቅታብናለች ብለዋል፡፡ እናም ዩክሬናዊያን አየሩ ሰላም እስኪሆን ድረስ ለደህንነታችሁ ጥሩ በሆኑ ስፍራዎች ተሸሸጉ በማለትም ለዜጎቿቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

ባለስልጣናቱ በሰሜንምስራቅ ዩክሬን በድሮን ጥቃት የሰው ህይወት መቀጠፉን ተናግረዋል፡፡ ሩሲያ በዚህ ጥቃት ሰባት የባላስቲክ ሚሳኤሎችን እና 239 ድሮኖችን መጠቀሟም ተነግሯል፡፡

ከዚህ ሳምንት ቀደም ብሎ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባደረሰችው ጥቃት 11 ዩክሬናዊያን የተገደሉ ሲሆን፤የ100 ዓመት ዕድሜ ያለውና በዩኔስኮ የታሪክ ቅስነት የተመዘገበ ገዳም ውድሟል፡፡

እነዚህ ከፍተኛ ጥቃቶች እየተፈጸሙ ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሩሲያ ወደ ድርድር ጠረጼዛው እንድትመጣ እንዲደረግና አራት ዓመታትን ያስቆጠረው ጦርነት እንዲጠናቀቅ ጫና እንዲደረግ እየጣሩ ባለበት ስዓት ነው፡፡

ዘለንስኪ በቡድን ሰባት አገራት ስብሳባ ላይ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ፡ማክሮን እና ከሌሎች መሪዎች ጋር ጦርነቱን ማስቆም በሚቻልበት ሁኔታ ትብብር እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ወደ ስልጣን እንደተመለሱ በ24 ስዓታት እንደሚቋጩት ቃል መግባታቸው የሚታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ በእኔ በኩል የሚቻለኝን አድርጊያለሁ እያሉ ነው፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe