የቀይ ባህር ስህተት ነገ ይታረማል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስሩ የህዳሴ ግድብ ምረቃን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በቀይ ባህር ላይ የተሰራው ስህተት በቀጣይ እንደሚታረም ገልጸዋል፡፡

ቀይ ባህር ከ30 ዓመታት በፊት በእጃችን ነበረ፤የተፈጠረውም ስህተት ትናትና ነው፤ነገ ይታረማል ብዙ ከባድ አይደለም በማለት ተናግረዋል፡፡

ጻጉሜ 4/2017 የሚመረቀውን የህዳሴ ግድብ አስመለክቶ ባደረጉት ንግግር የሺ ዓመታት የአባይ ታሪክ እንደተቀየረው ሁሉ ኢትዮጽያ የባህር በር ያጣችበት ሁኔታም እንደሚስተካከል ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም አባይ ከተራሮች ላይ አጥቦ ይወስድ የነበረው አፈራችንን ብቻ ሳይሆን ወርቃችንን ጭምር ነው ብለዋል፡፡

ገድቡ መገንባቱን ተከትሎ የተከማቸውን ደለል ስናስፈትሽ ወርቅ እያገኘንበት ነው ብለዋል፡፡ በዚህ ስዓት ግድቡ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ውሃ መያዙ ተነግሯል፡፡

ታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ ይመረቃል መባሉን ተከትሎ ግብጽ እክል ለመፍጠር እየተሯሯጠች እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe