ሙሉጌታ ከበደ የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጽያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ ተጫዋች የነበረ ነው፡፡ በዚህ ስዓት የአንድ እግሩ ጣት ተቆርጦ እስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው ቤተ ዛታ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በተጫዋችነት ዘመኑ ደማቅ ስም የነበረው ሙሉጌታ ከበደ የህመሙ ምክንያት ባይታወቅም የአንድ እግር ጣቱ መቆረጡ ነው የታወቀው፡፡ ሙሉጌታ ከበደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች በነበረበት ወቅት በ15ኛው የመካከለኛውና የምስራቅ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ላይ ታሪክ በመስራት እግር ኳስ ወዳዱን ህዝብ ማስደሰት ችሎም ነበረ፡፡ ሙሉጌታ ከበደ ለረጅም ዓመታት በአሜሪካን ሀገር የቆየ ሲሆን በዚያም ታዳጊ ወጣቶችን እግርኳስን ሲያለሰልጥን ቆይቷል፡፡ ወደ ኢትዮጽያ ከተመለሰ በኋላ ኑሮውን ለማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢ ፕሮግራም ቢዘጋጅለትም በቂ የሆነ ድጋፍ አለማግኘቱ ይታወሳል፡፡ ሙሉጌታ ከበደ በ1977 እና 78 ዓ.ም የኢትዮጽያ ከፍተኛ ዲቪዚዮን ውድድር ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ መሸለሙ ይታወሳል፡፡
ይህ የቅዱስ ጊዮርጊስና የኢትዮጽያ ብሔራዊ ቡድን ባለውለታ በዚህ ስዓት በጠና ታሞ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

