የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዙአቤ በ2022 የምርጫ ቅስቀሳ ላይ በነበሩበት ጊዜ ነበር ግለሰቡ በጥይት ተኩሶ የገደላቸው፡፡ በወቅቱም ግለሰቡ ወዲያውኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል ጠባዎች አማካኝነት መያዙም ይታወሳል፡፡ የግለሰቡ ጠበቃዎች ግለሰቡ በ20 ዓመት እስራት እንዲቀጣ የጠየቁ ቢሆንም ውድቅ ተደርጓል፡፡ ገድያው የተፈጸመው ግለሰቡ በቤተሰብ ችግር ምክንያት በደረሰበት ከፍተኛ የአዕምሮ ውጥረት እንደሆነ በመጥቀስ ጠበቃዎቹ ተከራክረዋል፡፡
ለዚህም ምክንያቱ የወንጀለኛው ግለሰብ ወላጅ እናት ዩኒቪኬሽን ቸርች ተብሎ ለሚጠራው የሃይማኖት ቡድን በነበራት ታማኝነት የተነሳ ቤተሰቡ ለከፍተኛ ችግር በመጋለጡ ነው እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የተከሳሹ እናት ንብረቷን በሙሉ ለዚህ ድርጅት በመስጠቷ ቤተሰቡ ለኪሳራ መዳረጉ ተነግሯል፡፡
በዚህ መሠረት ግለሰቡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ አቤ ከዚሁ የሃይማኖት ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ብሎ በማመኑ መሆኑን ታስ አስነብቧል፡፡//

