የቅርንፉድ (Cloves) እጅግ ግዙፍ የጤና ጥቅሞች

በኩሽናችን ውስጥ ያለችው ይህቺ ትንሿ ቅመም ምን ያህል ድንቅ የጤና ባለቤት እንደሆነች ታውቃላችሁ አይደል?ቅርንፉድ ለሆድ መነፋትና ለአጠቃላይ ጤና ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት በውስጡ ባለው የዩጂኖል (Eugenol) ንጥረ ነገር አማካኝነት ነው። እስቲ ዛሬ ስለ ቅርንፉድ አስደናቂ ጥቅሞች እና አጠቃቀም አብረን እንይ ተከተሉኝጋዝን ያጠፋል፡ ከባድ ምግብ ከተመገብን በኋላ የሚሰማንን የሆድ መክበድ እና ጋዝ በፍጥነት ያረጋጋል።
መፈጨትን ያፋጥናል፡ የምግብ መፈጨት ሥርዓትን በማነቃቃት ምግብ በቀላሉ እንዲሰባበር ያደርጋል።
ለአፍ ጤና፡ ባክቴሪያዎችን በመዋጋት መጥፎ የአፍ ጠረንን ያጠፋል፣ የጥርስ ሕመምን ያስታግሳል።
የበሽታ መከላከል አቅም፡ በፀረ-ኦክሲዳንት የበለፀገ በመሆኑ ሰውነታችንን ከበሽታ ይጠብቃል።
 አጠቃቀም አማራጮች
1,የቅርንፉድ ሻይ፡ 2 ፍሬ ቅርንፉድ በሙቅ ውሃ ውስጥ ለ 5 ደቂቃ ዘፍዝፎ፣ ትንሽ ማር ጨምሮ መጠጣት።
2,በባዶ ሆድ ማኘክ፡ ጠዋት ላይ 1 ወይም 2 ሙሉ ቅርንፉድ በቀስታ ማኘክ (ለአፍ ጠረን እና ለሆድ መነፋትን ለማስታገስ ይጠቅማል)
3,የቅርንፉድ ውሃ፡ 3-4 ቅርንፉድ በአንድ ብርጭቆ ውሃ ውስጥ ሌሊቱን ዘፍዝፎ ጠዋት በባዶ ሆድ መጠጣት።
 ማሳሰቢያ ፡ ቅርንፉድ ኃይለኛ ስለሆነ በቀን ከ 2-3 ፍሬ በላይ መጠቀም የለብንም። ነፍሰጡር ከሆናቹ ወይም መድኃኒት የምትጠቀሙ ከሆነ መጀመሪያ የጤና ባለሞያ አማክሩ።
የሚቀጥለው post በናንተ ምርጫ ነው ስለ ቅርንፉድ ሌላ አስደናቂ ሚስጥር ይዤላችሁ እንድመጣ የትኛውን ትመርጣላቹ? በኮሜንት ምርጫችሁን አሳውቁኝ፡
A) ለላቀ ውበት (ለፈጣን የጸጉር እድገት እና ለፊት ቆዳ ጥራት አጠቃቀሙ)
B) ለክብደት መቀነስ (ቦርጭን ለማጥፋት እና ስብን ለማቃጠል ያለው ሚና)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe