የበእውቀቱ ስዩም ግጥሞች በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉመው ታተሙ

የበእውቀቱ ስዩም ግጥሞች በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉመው ታተሙ

የወጣቱ ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም የተመረጡ የግጥም ስራዎች ወደ ፈረንሳይኛ ተተረጉመው የታተሙ ሲሆን በቅርቡ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በደማቅ ስነ ስርአት እንደሚመረቅ ተነገረ፤

ከዘመናዊ የኢትዮጵያ ወጣት ገጣሚያን መሀከል አንዱ የሆነው በእውቀቱ በአጫጭር ግጥሞቹ ጥልቅ የህይወት ፍልስፍናዎችን የመግለጽ ብቃት ያለው ገጣሚ ሲሆን ግጥሞቹ ተመርጠው በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉመው መታተማቸው የሁለቱን ህዝቦች ባህል ይበልጥ ለማቀራረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ታምኖበታል፤

እንደ ሞሊየርና ቪክቶር ሂጎ አይነት የተለያዩ የፈረንሳይ ደራሲያን ስራዎች ቀደም ባለው ጊዜ ወደ አማርኛ ተተረጉመው ለህዝብ የቀረቡ ሲሆን ከኢትዮጵያ ድራሲያን መሀከል የግጥም ስራዎቹ ወደ ፈረንሳይኛ ተተረመው ሲታተም በእውቀቱ ስዩምን የመጀመሪያው ኢትዮጰያዊ ገጣሚ ያደርገዋል፤

ወደ ፈረንሳይኛ ተተረጉመው የታተሙት የበእውቀቱ ግጥሞችን የያዘው መጽሃፍ የፊታችን ጥቅምት 22 ቀን 2016 በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚዘጋጅ ፕሮግራም ላይ የፈረንሳይ ገጣሚያንና የዩኔስኮ ከፍተኛ አመራሮቸ በሚገኙበት የሚመረቅ ሲሆን በሳምንቱ ብራስልስ በሚገኘው የሮያል አካዳሚ የቤልጂየም ንጉሳውያን ቤተሰቦችና ጥሪ የሚደረግላቸው ታላላቅ እንግዶች በሚገኙበት የግጥም ምሽት ላይ በእውቀቱ ተገኝቶ ግጥሞቹን እንደሚያቀርብ ታውቋል፤ በቤልጂየም ሩያል አካዳሚ ኦፍ ብራስልስ የስነ ጽሁፍ ስራዎቻቸውን የሚያቀረቡ ደራሲያን በአለም አቀፍ መድረኮች ላይ ሰፊ ተቀባይነት የሚኖራቸው ከመሆኑም በላይ የበእውቀቱ ስራዎች በፈረንሳይኛ ተተረጉመው መቅረባቸው እንደ ኖቤል ባሉ ታላላቅ የሽልማት አዘጋጆች የመታየት እድላቸውን ያሰፋዋል ተብላል፤

ከዚህ በፊት የበእውቀቱ ግጥሞች ወደ እንግሊዝኛ ተተረጉመው ታትመዋል፤ ይህ ወደ ፈረንሳይኛ የተተረጎመው መጽሃፍም በአማርኛ ታተሞ በሻማ ቡክ በኩል በቅርቡ ለገበያ እንደሚቀርብ ቁም ነገር ተረድታለች፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe