የበጎ ሰው ሽልማት በበጀት እጥረት ሳቢያ ሊቋረጥ መሆኑ ተሰማ

የዘንድሮው የበጎ ሰው የሽልማት መርሃ ግብር በፋይናንስ እጥረት ሳቢያ ላይካሄድ እንደሚችል ተሰማ፡፡
ላለፉት 12 ዓመታት በዓመቱ መጨረሻ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች ላይ በጎ አስተዋፅኦ ላደርጉ ሰዎች የሚሰጠው ሽልማት ድርጅቱን በሚደግፉ ተቋማት የፋይናንስ እጥረት ሳቢያ የመቋረጥ አደጋ እንዳጋጠው ተነግሯል፡፡
የበጎ ሰው ሽልማት ላለፉት 10 ዓመታት ስፖንሰር በማድረግ ሽልማቱን ሲደግፍ የቆየው ሄኒከን ኢትዮጵያ የቢራ ማስታውቂያ በብሮድካስት ሚዲያዎች እንዳይተላለፍ መታገዱን ምክንያት በማድረግ የበጎ ሰው ሽልማት መርሃ ግብር በቀጥታ ስርጭት በቴሌቪዥን በሚተላለፍበት ወቅት ሽልማቱን ስፖንስር ከሚያደርግበት በጀት ጋር የማይመጣጠን ማስታስታወቂያ ሽፋን በመሰጠቱ የተነሳ የስፖንሰር ድጋፉን ማቋረጡ ታውቋል፡፡
የበጎ ሰው ሽልማትን እንደ ቴሌና ንግድ ባንክ ባሉ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ስፖንስር ለማስደረግና ለማስቀጠል የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ የዘንድሮ የበጎ ሰው ሽልማት ላይካሄድ እንደሚችል ታውቋል፡፡
የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ የተመዘገበና በበጎ ፈቃደኛ የቦርድ አባላት የሚተዳደር ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዓመታዊ የሽልማት በጀቱን አሁንም በለጋሾች ድጋፍ ነው የሚያካሂደው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe