ሁሉ አቀፍ የተሸከርካሪ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል የሚሰጥ በ50 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ፕሮጀክት ፀድቆ ወደስራ ሊገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስትና የግል አጋርነት ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
ፕሮጀክቱ በመንግስት የግል አጋርነት የሚሰራ ሲሆን በተበታተነ መልኩ ሲሰጥ የነበረውን የተሸከርካሪ ሽያጭ፣ የባንክና ኢንሹራንስ፣ውል እንዲሁም ቦሎ ና የመሳሰሉትን የከተሸከርካሪ አገልግሎቶችን በአንድ መዓከል ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስትና የግል አጋርነት ፅ/ቤት የኮሚኒኬሽንና የአቅም ግንባታ ጉዳይዎችች ከፍተኛ አማካሪ ዋጋዬ ተስፋዬ ናቸው፡፡
ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር አንድ ተሽከርካሪ ገዥው እጅ እስኪገባ ድረስ ይወስድ የነበረውን የገንዘብና የጊዜ ብክነት ይቆጥባል ብለዋል፡፡
ማዕከሉ አገልግሎት በአዲስ ተሸከርካሪ ብቻ ሳይወሰን የፍተሻ፣ ጥገና እንዲሁም ሙሉ የጋራዥ ስራዎች የሚሰራበት ይሆናል ሲሉም ጠቁመዋል፡፡
ለዚህ አገልግሎት የሚውለውን 50 ሄክታር መሬት መንግስት የሚያቀርብ ሲሆን በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ አማካሪው ገልፀዋል፡፡

