ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ የቶታል ኢነርጂስ አራተኛ ዙር የአመቱ ምርጥ አዲስ ስራ ፈጣሪ ውድድር የሀገር ውስጥ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል።
በሀገር ውስጥ 719 ተወዳዳሪዎች ተመዝግበው 14ቱ የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ፕሮጀክቶቻቸውን ለሀገር ውስጥ ዳኞች አቅርበው አሸናፊዎች መለየታቸው ተገልጿል።
የአመቱ ምርጥ አዲስ ስራ ፈጣሪ ውድድር በሶስት ዘርፎች አሸናፊዎች መካከል በ “ኢኖቭ አፕ” ምድብ ለገበሬዎች ጊዜና ድካምን የሚቀንስ በፀሀይ ኃይል የሽንኩርት ስርና ቅጠል ማንሻ ሶላር መቀስ የሰራው ተወዳዳሪ ምርጡ ስራ ፈጣሪ ተብሏል።
በ”ሳይክል አፕ” ምድብ የፕላስቲክ ቦርሳዎችን በመተካት ለአካባቢ ተስማሚ በሆነ መልኩ የሚሰራ “ኤኮ ፓኬጅ እና ቦርሳ” የተባለ መሳሪያ የሰራው ተወዳዳሪ ምርጥ የኢኮኖሚ ፕሮጀክት ተብሏል።
እንዲሁም “በፓውር አፕ” ምድብ ከቡና ገለባ ተረፈ ምርት እና ከተፈጥሮ በተገኘ መቀላቀያዎች / ተፈጥሮአዊ ንጥረ ነገሮች አረንጓዴ ኢንርጂ ያመረተ ተወዳዳሪ ምርጡ ዘላቂ እና ተመጣጣኝ የባዮ ጄል ነዳጅ ተሸላሚ ሆኗል።
የውድድሩ አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 432 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ያገኙ ሲሆን ፕሮጀክታቸውን ወደተግባር መቀየር የሚያስችላቸውን ድጋፍ እንደሚያገኙም ተገልጿል።
ለስራ ፈጣሪ ውድድሩ 32 ሀገራት እና 14 ሺህ የተሟሉ ማመልከቻዎች ተሳትፈዋል ተብሏል።

