#Ethiopia : ርእሰ መስተዳድሩ ፓርቲያቸውን ብልጽግና ወክለው ነው በጎንደር ከተማ አስተዳደር በሚገኘው ምርጫ ክልል ሁለት በእጩነት የተመዘገቡት።
አቶ አገኘሁ በምርጫ ክልሉ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በመጭው ሀገራዊ ምርጫ ለመወዳደር የተለያዩ ፓርቲዎች ከየካቲት 2/2013 ዓ.ም ጀምሮ የመለያ ምልክታቸውን በማሳወቅ የምረጡኝ ዘመቻ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። እርሳቸውም የምርጫ ሂደቱን ጠብቀው የጎንደር ከተማ ሕዝብ በመወከል በፓርቲያቸው ለክልል ምክር ቤት ለመወዳደር እንደተመዘገቡ ነው ያሳወቁት።
በምዝገባው ወቅት የምርጫ ክልሉ ሠራተኞች በአግባቡ እንዳስተናገዷቸውም ጠቁመዋል።
ከዲሞክራሲያዊ ምርጫ አንጻር እጩዎች ሂደቱን ጠብቀው መመዝገባቸው ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ነው ያስረዱት አቶ አገኘሁ።
ፓርቲያቸው የጎንደር ከተማን ሕዝብ ወክለው ለመወዳደር እጩ ስላደረጋቸውም አመስግነዋል።
በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ከአደጉበት ማኅበረሰብ ጋር በአካል ተገናኝተው በጋራ እንደሚሠሩም አሳውቀዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን አንድም እንደ መንግሥት ሁለትም እንደ ፓርቲ ኀላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
የምርጫ ጣቢያዎች ሥራቸውን ለመሥራት የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት በማሟላት ሥራቸውን በተሳካ ሁኔታ የሚሠሩበት ሂደት እየተፈጠረ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምርጫ ክልል ሁለት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ካሳይ እስካሁን በምርጫ ክልሉ የተመዘገቡ እጩ አቶ አገኘሁ መሆናቸውን በመጠቆም ሌሎች 3 እጩዎች በቀሪ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር የጎንደር ከተማ ሕዝብን ወክለው ለክልል ምክር ቤት ለመወዳደር በእጩነት ተመዘገቡ

