የአማራ ክልል ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ የግዕዝ ቋንቋን ማስተማር ሊጀምር እንደሆነ ተሰማ

በክልሉ ከመጪው የትምህርት ዘመን ጀምሮ ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የግዕዝ ቋንቋ መሰጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡

የአማራ ክልል ከ2015 ጀምሮ የግዕዝ ቋንቋን በሙከራ ደረጃ ሲያስተምር እንደቆየ ተመላክቷል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም የዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች በጻፈው ደብዳቤ ትምህርቱን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ አሳስቧል፡፡

በ2017 ዓ.ም በክልሉ 16 ዞኖች እና በ45 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና መለስተኛ ትምህርት ቤቶች ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ የግዕዝ ቋንቋን በመደበኛነት ሲሰጥ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

በመምህራን እጥረት ምክንያት በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ቋንቋውን ማዳረስ ሳይቻል መቅረቱ ተገልጻል፡፡

በትምህር ፖሊስ መሠረት ተማሪዎች ተጨማሪ ቋንቋ እንዲማሩ የሚፈቅደው ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ በመሆኑ ትምህርቱ ከዚህ የክፍል ደረጃ ይጀምራል ነው የተባለው፡፡

የግዕዝ ቋንቋ በዓለማችን ረጅም እድሜ ካስቆጠሩ ጥናታዊ ቋንቋዎች አንዱ ሲሆን፤በኢትዮጽያ ለሚነገሩ በርካታ ቋንቋዎች መሠረት እንደሆነም ይነገራል፡፡

የማስተማሪያ እና መማሪያ መጽሐፍቶች ሥርዓተ ትምህርቱ እስከ 6ኛ ክፍል ተሰናድቶ ለሕትመት መዘጋጀቱም ተነግሯል።

የግእዝ ቋንቋ እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት የሚሰጥ ቢሆንም፣ በስምንተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውስጥ ለጊዜው እንደማይካተት ታውቋል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe