የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በግሪንላንድ እና በካናዳ ላይ አዲስ የቃላተ ጦርነት ከፍቷል፡፡ አስተዳደሩ ግዛቶቻችሁን ስጡን በማለትም ቀጥሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸውን እንደጀመሩ የዓለምን የፖለቲካ መድረክ በሚያናውጡ እቅዶች ብቅ ማለታቸው ይታወቃል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የአሜሪካ የቅርብ ወዳጅና ጉረቤት የሆኑትን ግሪንላንድን እና ካናዳን የአሜሪካ አካል እናደርጋለን የሚሉ የይገባኛል ጥያቄችን በባለሥልጣኖቻቸውም ይሁን በራሳቸው አንደበት እየተናገሩ ነው፡፡
ይህ የእርሳቸው አካሄድ በሀገራቱ መካከል መደናገጥንና ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ በምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተናገሩት ንግግር የዴንማርክ ባለስጣናትን ክፉኛ አስደንግጧል፡፡
ሩቢዮ ግሪንላድ የዴንማርክ አካል ሆና የምትቀጥለው ለአሁኑ ብቻ ነው በማለት በትራምፕ ልብ ውስጥ ያለውን የተደበቀ ምኞት ይፋ አድርገዋል፡፡ የአሜሪካ ጦር እ.ኤ.አ 1951 ጀምሮ በደሴቷ ላይ ወታደራዊ መሸጋገሪያ ቢኖረውም የዴንማርክ እና የግሪንላንድ መሪዎች ግን በአንድ ድምጽ ግሪንላንድ ለሽያጭ የቀረበች ድርጅት አይደለችም ሉዓላዊ ሀገር ናት በማለት የትራምፕን የግዢ ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡
ትራምፕ ካናዳን 51ኛዋ የአሜሪካ ግዛት እያሉ መጥራት ከጀመሩ ትንሽ ሰንበትበት ማለታቸው ይታወቃል፡፡//
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ግሪንላድ የዴንማርክ አካል ሆና የምትቀጥለው ለአሁኑ ብቻ ነው ማለታቸው ድንጋጤ ፈጠረ

