የአሳ ዘይት ለህፃናት የሚሰጣቸው ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች

የአሳ_ዘይት (Fish Oil) በውስጡ በያዘው ከፍተኛ የኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ (DHA እና EPA) አማካኝነት ለህፃናት #የአእምሮ፣ የዕይታ እና የባህሪ ዕድገት እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ የተፈጥሮ ማሟያ ነው። #የአሳ_ዘይት ለህፃናት የሚሰጣቸው ዋና ዋና የጤና ጥቅሞች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡

  1. የአእምሮ ዕድገትና የማስታወስ ችሎታን ማሻሻል የአሳ ዘይት በውስጡ የያዘው DHA የተባለው ንጥረ ነገር የአእምሮ ሴሎች እንዲገነቡና በትክክል እንዲሰሩ ይረዳል። የህፃናትን የማስታወስ፣ የማሰብ እና አዳዲስ ነገሮችን የመማር ብቃት ያሳድጋል። በትምህርት ቤት ውስጥ ያላቸውን የትኩረት መጠን ይጨምራል።
  2. የባህሪ መስተካከል እና የADHD ምልክቶችን መቀነስ ትኩረት የመንሳት እና ከልክ በላይ መቅበጥበጥ (ADHD) ችግር ላለባቸው ህፃናት የአሳ ዘይት ትልቅ እገዛ ያደርጋል። የህፃናትን ከልክ ያለፈ መቅበጥበጥ እና ግልፍተኝነት ይቀንሳል። እረፍት የመንሳት ስሜትን በማስታገስ ረገድ ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋግጧል።
  3. ለአይን ጤንነት እና ለዕይታ ጥራት የዓይን ብሌን (Retina) መዋቅር በተገቢው ሁኔታ እንዲያድግ ኦሜጋ-3 ወሳኝ ነው። የህፃናትን የማየት ብቃት (Visual Acuity) ያሻሽላል። ዓይን እንዳይደርቅና እንዳያብጥ ይከላከላል።
  4. ጥራት ያለው እንቅልፍ እና የተረጋጋ ስሜት በሰውነት ውስጥ የኦሜጋ-3 መጠን ዝቅተኛ መሆን ከእንቅልፍ መቆራረጥ ጋር ይያያዛል። ህፃናት ለረጅም ሰዓትና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲተኙ ያደርጋል። የህፃናትን የድብርት እና የጭንቀት ስሜት በመቀነስ መልካም ስሜት (Mood) እንዲኖራቸው ይረዳል።
  5. የሰውነት መከላከያ አቅምን ማጠናከር የህፃናትን የሰውነት መከላከያ ስርዓት (Immunity) በማጠናከር ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች እንዳይጋለጡ ያደርጋል። እንደ አስም (Asthma) እና አለርጂ ያሉ የጤና እክሎችን የመከላከል አቅም አለው።
  6. ምንጪ -ethio tena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe