የአቮካዶ ምርት ላይ በተሰሩ ሥራዎች ከአንድ ዛፍ በአማካኝ እስከ 50 ኪሎ ድረስ እየተመረተ ነው።
በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የአቮካዶ ምርት በስፋት እንዲመረትና ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸው ሲገለጽ ቆይቷል።
ከአቮካዶው ፍሬ ለማግኘት ሦስት አመታትን በትዕግስት መንከባከብ ይጠይቃል። የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲም ይህንኑ ሥራ ሲደግፍ መቆየቱን ገልጿል።
በዚህ ሥራ ከተሰማሩ አርሶ አደሮች አንዱ አርሶ አደር አቶ አሸናፊ አያሌው ማሳ ናቸው። አርሶአደሩ ያመረቱትና በውጪ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው ሃስ የአቮካዶ ዝርያ ከአንድ ዛፍ በአማካኝ እስከ 50 ኪሎ ድረስ እንደሚገኝበት ይናገራሉ።
የአቮካዶ ምርት እንደሌሎች የሰብል አይነቶች ጎተራ ገብቶ ገበያ እስከሚገኝ ለመጠበቅ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም፤ ይህንን ታሳቢ አድርጎ የገቢያ ትስስር መሰራቱን ኤጀንሲው ገልጿል።
አሁን ላይ የአቶ አሸናፊና በተመሳሳይ ግዜ የተተከሉ የሌሎች አርሶአደሮች የሦስት ዓመት የሥራ ድካም ውጤት የሆነውን የአቮካዶ ምርት ለውጪ ገበያ እንዲውሉ በመሰብሰብ ላይ ይገኛሉ።

