አትሌት ገለቴ ቡርቃ ከሳምንት በፊት በሰይፉ ሾው ላይ ቀርባ ባለቤቴ በነበረ ሰው ንብረቴ ተዘረፈ ጉዳና ላይ ለመውጣት ጫፍ ላይ ደርሻለሁ ማለቷ ይታወሳል፡፡
በሩጫ የህይወት ዘመኔ አፈራዋቸሁ ያለችውን 11 ቤት እና አምስት ቤት ተዘርፌ ችግር ውስጥ ወድቂያለሁ ህዝብና መንግስት ይድረስልኝ ብላም ነበር፡፡
ይህንን ተከትሎም ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል፡፡ የአለትሌክስ ፌደሬሽንም ገለቴ ፍትህ እንዲሰጣት ማድረግ ይጠበቅብኛል የሚል ይዘት ያለው መግለጫ መስጠቱን እናስታውሳለን፡፡
ትላት እሁድ አትሌት ገለቴ ቡርቃ ቀርባ ብሶቷን ባቀረበችበት የሰይፉ ሾው ላይ ታደለ ቀርቦ የተባለው ነገር ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ብሏል፡፡
11 ቤትም ይሁን አምስት መኪና የለንም፤ኖሮንም አያውቅም ብሏል፡፡ ገለቴ ቡርቃ በግዥና ከመንግስት በስጦታ ያገኘሁትን 11 ቤትና መሬት እንዲሁም አምስት መኪኖች ውስጥ 10ሩን ቤትና አራቱን መኪኖችን ባለቤቴ በነበረው ታደለ ገ/መድህን በተባለው ሰው ተሸጦብኛል ማለቷ ይታወሳል፡፡
ይህንን በተመለከተ ምላሹን የሰጠው የቀድሞ የገለቴ ባለቤት ታደለ በነበረኝ ሙሉ ውክልና እሷ ሳታውቀው አንድም ነገር የተፈጸመ ነገር የለም ጊቢያችን ውስጥም አምስት መኪና ኖሮን አያውቅም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ከ2009 ዓ.ም በኋላ በትዳራችን ውስጥ በገጠመን አለመግባባት ፍቺ መፈጸም ስለፈለኩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስጄ ፍቺ ፈጽመናል ነገር ግን እርሷ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም በሚል ፍቺውን እንደማትፈልገው ገልጻ ነበር ነገር ግን በፍርድ ቤት መለያየት ችለናል ነው ያለው፡፡
በሩጫ ህይወት ያፈራኋቸው 11 ቤቶችንና አምስት መኪናዎችን በቀድሞ ባለቤቴ አጥቻለሁ በሚል ለቀረበበትም ክስ ጉዳያችን 7 ዓመት በፍርድ ቤት ተይዞ የቆየ ነው ከታችኛው ፍርድ ቤት እስከ ሰበር ድረስ ደርሶ የተወሰነ ውሳኔ ነው እኔ ምንም የወሰድኩባት ነገር የለም ሲል ተናግሯል፡፡
ገለቴ 2009 ከአሜሪካው ውድድሬ ስመለስ ባለቤቴን ከቤት አጣሁት ጸበል ሄጃለሁ የሚል መልዕክት አስቀምጦልኝ ነው የሄደው ብላ ነበር፡፡ ታደለ ይህንን ማድረጉን አምኖ ፍቺ መፈጸም ስለፈለገ ያንን እንዳደረገም ገልጻል፡፡
ስለዚህ እኔ የሸጥኩት 11 ቤትም ይሁን አምስት መኪና የለም ገርጂ አካባቢ እናቱ እንዲኖሩበት የሰጠኋቸውን ቤት ለእናቱ በ200ሺ ብር ሸጦታል ለተባልኩትም ቤቱ በግዥ እንጂ ከመንግስት በሽልማት መልክ ያልተገኘ መሆኑን አስታውሶ ለወላጅ እናቴ በስጦታ መልክ እንድንሰጣቸው ስሙም ወደ እናቴ እንዲዞር ያደረግነው ተስማምተን ነው ብሏል፡፡
ታደለ ገ/መድህን በአትሌት ገለቴ ላይ የግድያ ሙከራ ለማድረግ መሞከሩም በገለቴ በኩል ተገልጻል ነገር ግን ታደለ የግድያ ሙከራውን እንዳላደረገ ገልጾ ይልቁንም ተደጋጋሚ የግድያ ሙከራዎች በእኔ ላይ ደርሰውብኛል ብሏል፡፡
የሁለቱ አለመስማማት ጉዳይ በሽምግልና እንዲያልቅ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነ እየተሰማ ነው፡፡

