የአንጋፋው ጋዜጠኛና የኮሙኒኬሽን ባለሙያ እሸቱ ዱብ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

በጋዜጠኝነት፣ በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን፣ በቢዝነስ ስትራቴጂ፣ በሥነ ጽሑፍና በፊልም ዘርፍ የሚታወቁት አንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቱ ዱብ በ50 ዓመቱ  አርፋል።
ከ30 ዓመታት በላይ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ያገለገለው እሸቱ፣ በ1987 ዓ.ም. ፋና ሬዲዮ ሲመሠረት ከመጀመሪያዎቹ ባልደረቦች አንዱ በመሆን የመዝናኛ ክፍሉን በመምራት ዘርፉ ላይ የማይረሳ አሻራ አሳርፋል።
ከጋዜጠኝነት ባሻገር በኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን፣ ብራንዲንግ፣ ማርኬቲንግ እና የቢዝነስ ስትራቴጂ ዘርፎች በሰፊው ሠርተል።
በCRDA የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር፣ በዋፋ ማርኬቲንግ የብራንዲንግና መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ኃላፊ እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት አማካሪና አሠልጣኝ ሆነው አገልግለዋል።
በሥነ ጽሑፍ ዘርፍም “ቀይ ልበሽ” የግጥም መድበል እና “የቅርብ ሩቅ” የተሰኘ ተውኔትን ጨምሮ በርካታ ሥራዎችን አበርክተል።
በኢኮኖሚ፣ በፖሊሲና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጽሑፎቹም በስፋት ተነብበዋል።
በእውቀታቸው፣ በትህትናቸው፣ በሙያዊ ብቃታቸው እና ወጣት ጋዜጠኞችን በማብቃት በኢትዮጵያ ሚዲያ ዘርፍ ዘላቂ አሻራ አስቀምጦ አልፈዋል።
እሸቱ ዱብ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ሕይወቱ ማለፉ የተነገረ ሲሆን፣ የቀብር ሥነ ሥርዓቱም  ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በጣፎ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe