የአእምሮ ጤና ነገር በኢትዮጵያ ከ5 ሰው አንዱ ከአእምሮ ህመም ጋር ይኖራል!

ሰሞኑን ( ኦክቶበር 10) የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን ሲሆን “ በየስራ ቦታዎቻችን ለአእምሮ ጤና ቅድሚያ የምንሰጥበት ጊዜው አሁን ነው !” በሚል መሪ ቃል በመላው ዓለም  ተከብራል፤

በዓለም ላይ ከ1.5 ቢሊየን በላይ የሆኑ ሰዎች በአእምሮ ህመም ተጠቂ ሲሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ5 ሰዎች አንዱ/ዷ በህይወት ዘመናቸው ውስጥ በአዕምሮ ህመም የመያዝ እድል እንዳላቸው ይፋ ሆናል፡፡

ዛሬ የአለም የአእምሮ ጤና ቀንን ስናከብር በስራ ቦታችን ለአእምሮ ጤና ቅድሚያ እንስጥ በሚለው መሪ ቃል መሰረት መስሪያ ቦታዎቻችንን እንዲሁም አካባቢዎቻችንን ለአእምሮ ጤና የሚያግዙ ማድረግ  ያስፈልጋል፡፡

በሀገራችን ስለ አእምሮ ጤና ያለው ግንዛቤ አነስተኛ በመሆኑ በአእምሮ ጤና መታወክ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተወሳሰበ እና ዘርፈ ብዙ እየሆነ መጥተል፤ ችግሮቹ የሚሹት ምላሽም እንዲሁ ዘርፈ ብዙ በመሆኑና የአእምሮ ጤና ችግር እያደረሰው ካለው ጫና አንፃር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እየሰጡት ያለው ምላሽ አናሳ  ነው፡፡

የዓለም በሽታዎች ጫና መረጃ እንደሚያሳየው በዓለማችን የአእምሮ ህመም ስርጭት ከ1.5 ቢሊየን በላይ ሰዎች ተጠቂ ሲሆኑ በአህጉራችን በአፍሪካ ወደ 116 ሚሊዮን ያክል ሰዎች ከአእምሮ ህመም ጋር ይኖራሉ። ከዚህም ውስጥ የድባቴ ህመም ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ ከ5 ሰዎች አንዱ/ዷ በሕይወት ዘመናቸው ውስጥ በአዕምሮ ሕመም የመያዝ እድል አላቸው።

የአእምሮ ጤና  ህክምና ሆስታሎች ቁጥር አነስተኛ መሆን የችግሩን ስፋት ያሳያል፡፡ በእርግጥ የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአእምሮ ጤና ጋር በተያያዘ እንደ ሀገር ከአማኑኤል ሆስፒታል ቀጥሎ ፎረንሲክ ሳይካትሪ፣ በስፔሻሊቲና ሰብ ስፔሻሊቲ አገልግሎት በመስጠት በተመላላሽ እና ተኝቶ ህክምና በመስጠት የጎላ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች መስፋታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ  ለአእምሮ ጤና ህክምና የሚረዱ ስልጠናዎች አስፈላጊነታቸው አጠያያቂ አይደለም፡፡

ከአለም ህዝብ 60 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በስራ አለም ላይ እንደሆኑ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

በስራ ላይ ካሉት ሰራተኞች ውስጥም ግማሽ የሚሆኑት የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥማቸው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም  የዓለም የአእምሮ ጤና ቀንን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።

የስራ አለም ላይ ያሉ ሰራተኞች በሚገጥማቸው የአእምሮ ጤና ችግርም በየአመቱ 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚጠፋ ዶ/ር ቴድሮስ ጠቅሰዋል።

ሰራተኞችን ለአእምሮ ጤና ችግር የሚዳርገው ምንድነው?

–  ዝቅተኛ የስራ ክህሎት፣ ችሎታ እና አፈፃፀም

– ከመጠን በላይ የሆነ የሥራ ጫና፤ የሰራተኞች እጥረት፤ አድልዎ፣ መገለል፣ ጥቃትና ትንኮሳ

– ረጅም፣ ያልተገደቡ እና ተለዋዋጭ የስራ ሰዓቶች

– አሉታዊ ድርጊቶችን የሚደግፍ ድርጅታዊ ባህል

– ከሥራ ባልደረቦች በቂ ድጋፍ አለማግኘት

– በቂ ያልሆነ ክፍያ፣ የሚጋጩ የሥራ ፍላጎቶች የአእምሮ ጤና እንደሚያስከትሉ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።

ዶ/ር ቴድሮስ ስራ የመስራት እድሜ ላይ ከደረሱ ስድስት አዋቂዎች አንዱ የአእምሮ ጤና ችግር እንደሚያጋጥመው የገለፁ ሲሆን የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅ የሚደረገው ኢንቨስትመንት አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ችግሩን ለመከላከል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ምን መደረግ አለበት አሉ ?

° አሰሪዎች የአእምሮ ጤና ችግር የሚያስከትሉ ችግሮችን በመለየት ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር እንደሚገባቸው፤

° የድርጅት ኃላፊዎች ጭንቀት ያጋጠማቸውን ሰራተኞች እንዲለዩ፣ የስራ ቦታ ላይ የሚያጋጥም የአእምሮ ጤና ችግርን እንዲቀርፉ መስራት እንደሚገባቸው፤

° የስራ ከባቢን ለሰራተኞች ምቹ እንዲሆን ማድረግ፤ አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም ሰራተኞች በንቃት እንዲሰሩ የሚያስችል የስራ ከባቢ መፍጠር እንደሚገባ ዶ/ር ቴድሮስ ባስተላለፉት መልእክት ተናግረዋል።

ሰራተኞች የአእምሮ ጤና ችግር በሚገጥማቸው ጊዜም ሰዎችን ማውራት፣ ባለሙያ ማማከር ወይም እራሳቸውን ማረጋጋት እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ቴድሮስ ገልፀዋል።

የአዕምሮ ጤናና  ”የመዝናኛ ነገር”??

የዓለም የአዕምሮ ጤና ቀን ሰሞኑን ሲከበር የአዕምሮ ህመም አይነቶች በርካታ መሆናቸው ተነግሯለ። ቀላል ከሚመስለው ድብርት (ድባቴ)ን ጨምሮ ሌላም ሌላም  እክል ኑራ ኢማም ትገልጣልች፡፡። አይነቱንም ሆነ መንስኤዎቹን ብሎም ተጨማሪ ነጥቦችን ባለሙያዎች በስፋት ይጠቅሱታል፡፡

በልማድ እና በተለያዩ አመለካከቶች መነሻ የሆነው  ”መዝናናት”ትርፍ እንጂ ዋናው የህይወት አካል ተደርጎ አይቆጠርም። ሰዎች ምን ያዝናናቸዋል? የሚለውን አይነቱን እንደእነሱ ምርጫ ትተን በመሰረታዊነት መዝናናት ዋና እንጂ ትርፍ ያለው ነገር አይደለም።

በአንድ ወቅት ኮሜዲያን ደረጄ ሀይሌ አንድ ንግግርን አድርጎ ነበር። ሁሌም አስበዋለሁ ” ሰውን ከማስለቀስ ይልቅ ማሳቅ በጣም ከባድ ነው። ለማሳቅ ተጨማሪ ልፋት ይጠይቃል”ብሎ ነበር። እዚህ ንግግር ውስጥ ከስሜት ጋር ያለው ትስስር በደንብ ተገልፇል ብዬ አምናለሁ። ስሜት ደግሞ በተሰጠው ነገር ልክም ውጤቱን ይሰጣል ስል አስባለሁ።

አዕምሮ እንክብካቤን ይፈልጋል። በ”ሀላፊነት በማሰብ” እና ባለመዝናናት” መካከል ልዩነት አለ። አለመዝናናት በራሱ ሀላፊነት የሚሰማው ሰው ልዩ ምልክት ነው ብዬ አላምንም። ዓይነቱን መጠኑን ሁኔታውን መምረጥ ግን ለየሰው የሚተው ነገር ነው።

አንድ ሰው ኳስን ለ 90 ደቂቃ ሲያይ ከህይወቱ ላይ ”90 ደቂቃ እያባከነ ” እንደሆነ ብቻ ሳይሆን ለአዕምሮውም ፋታ እየሰጠ ነው። ”በዛ ደቂቃ አትሰራበትም? ” የሚሉ ሀሳቦችን ሰምቼ አውቃለሁ። የመጠን ጉዳይ ከሆነ ሀሳባችን መዝናናት ብቻ ሳይሆን ስራም ከበዛ የራሱ የሚያመጣው ተፅዕኖ አለ ልክ አለመስራት የሚያመጣው ችግር እንዳለ ሁሉ ያልተመጠነ ማንኛውም ነገር ችግር አለው። ምግብም ከልክ ካለፈ ህመም አለው፣ይሄ መርህ ነው።

ፊልምም ይሁን ኳስም የሚያዩ ሰዎች የትርፍ ጊዜ ባለቤቶች እና የቅንጦት አለቆች አይደሉም። አንድ ሰው ለብቻው ከራሱ ጋር የተወሰነ ቁጭ ብሎ ማሳለፍም መዝናኛው ሊሆን ይችላል። አንተን ያላዝናናህ ነገር ለሌላው ሰው የቅብጠት መለኪያው መደረግም የለበትም። ፎቶ ማንሳት ስራውም መዝናናቱም ለሆነ ሰው ፎቶ ማንሳቱ ” አንተ ምን አለብህ? ”በሚል ሊያስወቅሰው አይገባም ብዬ አምናለሁ።

ራስንም ሆነ ሌላውን ሳይጎዱ ይዝናኑ፣ መዝናናት መጉዳት ሲጀምር ሌላው ነገሩ ሳይሆን ራሱ ማዝናናት የሚለው ትርጉሙ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይገባል።

አዕምሮ የተመጣጠነ ተገቢው እንክብካቤ ያስፈልገዋል። ተገቢው ትኩረት ለአዕምሮ ጤና ሊሰጥ ይገባል፡፡ በአዕምሮ ጤና ዙሪያ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለሚሰነዘሩ ”ቀልዶች”(ቀልድ የሚለው ተሰምሮበት) ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡

”ቀልድ” ከማዝናናቱም ባለፈ በመቀለዱ ውጤቱ ምንድነው?? ምንስ አመጣ? ከሚል አንፃር ነው መታየት ያለበት ብዬ አምናለሁ። አንዳንድ ነገሮችን ቀለል ማድረግ አሪፍ ነው። የማይቀለው ላይ ደግሞ ጠንከር ማለት ነው(ጉዳይ ማቅለል እና ነገር ማቅለል ይለያያል) ። አንዳንዴ በመደበኛ ህይወታችን የምንስቅባቸው ነገሮች ወደ ማህበራዊ ገፅም መተው ቢሳቅባቸው ችግሩ አይታየኝም። (ቀልድ ውስጥ መቀለዱ ያስከተለው የሞራል የሰው ክብር እና መሰል ጉዳት ተመዝኖ ካለፈ ቀልድም የህይወት አካል ነው ብዬ አምናለሁ)

በተደጋጋሚም እንደምለው የማይቀለድባቸው አሳዛኝ የሆኑ ነገሮች አሉ፤ እነሱ ላይ አሁንም ቀይ መስመር አለኝ(ከዛስ?) ለምሳሌ ያህል ለቅሶ ቤት ውስጥ ስለተሳቀ የሳቁት ሰዎች አላዘኑም ማለት አይደለም። በተቃራኒው አስክሬን እየወጣ ቦታውም ላይ መሰል ሁኔታዎች ላይ መሳቅ ግን ምንም ምንም ማለት ሳያስፈልገው ትክክል አይመጣውም። ቦታ እና ሁኔታን ለያይቶ ማየት ነው።

”በመሬት መንቀጥቀጡ(ንዝረት) ” ዙሪያ የቀለዱ ሰዎች መሬቱ በመንቀጥቀጡ አልያም በፈጣሪ ስራ ስለማያምኑ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ድንጋጤው ሁኔታው በፈጠራቸው ወይም ሊፈጥራቸው ይችላሉ ተብለው በሚታመኑ ክንውኖች (ነገሮች) ፈገግ ለማለት መሞከር ግን ለአዕምሮ ጤናም አስፈላጊ ነው።

ሁሉም ነገር አይከርም፣ሁሉም ነገር አይቀልም።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe