የአወሮፓ መሪዎች የ90 ቢሊዮን ዩሮ ለዩክሬን በብድር ለመስጠት ወስነዋል፡፡ ውሳኔውን የታቀወሙት የህብረቱ አባል ሀገራት እንዳሉም ተሰምቷል፡፡ ሀንጋሪ፡እስሎቫኪያ እና ቼክሪፐብሊክ ለዩክሬን እንዲደረግ የተወሰነውን ድጋፍ ተቃውመዋል፡፡
የሀንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪኪቶር ኦርባን በአውሮፓ የፕሬዝዳንት ፑቲን የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሰው ናቸው፡፡ ገንዘብ መስጠት ማለት ጦርነቱን ማስቀጠል ማለት ነው የሚል አስተያየት በመስጠት ውሳኔውን ተቃውመውታል፡፡
እነዚሁ መሪዎች በአውሮፓ የታደገውን በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠረውን ገንዘብ ለዩክሬን መስጠት ያስፈልጋል በሚል በሰፊው ሲወያዩ መክረማቸው ይታወቃል፡፡
አሁን ዩክሬን የመከላከያ አቅሟን እንድታጠናክር የ90 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር መወሰናቸውን ዛሬ አስታውቀዋል፡፡
የአውሮፓ መሪዎች ዩክሬን አቅሟን እንድታጠናክር ነው የ90 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ካለወለድ እንዲሰጣት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል የተባለው፡፡ ከዚህ ቀደም ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጎ ያለውን የሩሲያን ገንዘብ ለዩክሬን መሰጠት አለበት የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ በጊዜ ሂደት ግን ነገርየው የሙያመጣውን ፖለቲካዊ እና የህግ ጣጣን በመፍራት ለጊዜው ይህን ሀሳብ ተወት አድርገውታል፡፡
ይህ ገንዘብ ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ዩክሬን ወታደራዊ ፍላጎቷን እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቿን ለማሟላት የሚያግዛት መሆኑን የህብረቱ ካውንስል ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ ተናግረዋል፡፡
ይህ ውሳኔ የተሰማው ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሞስኮ መጪው 2026 አዲሱን ዓመት ሌላ የጦርነት ዓመት ለማድረግ እየተዘጋጀች ነው በሚል ከተናገሩ አንድ ቀን በኋላ ነው፡፡
በተጨማሪም ዘለንስኪ የአውሮፓ ህብረትን ማምስገናቸውን አልጀዚራ አስንብቧል፡፡ ድጋፉ የሚያጠናክረን ነው ሲሉም በኤክስ ገጻቸው ላይ አጋርተዋል፡፡ በአውሮፓ የሚገኘው የሩሲያ ሃብት መታገዱ ጥሩ ነው በሚል ገልጸው የተገኘው የገንዘብ ብድር ዩክሬን ለመጪዎቹ ሁለት ዓመታት በፋይናስ አኳያ ዋስትና እንድታገኝ ያደርጋታል ብለዋል፡፡
ህብረቱ ይህን የገንዘብ ብድር ለዩክሬን ለመስጠት ሲወስን በአውሮፓ የታገደውን የ250 ቢሊዮን ዶላር የሩሲያን ገንዘብ እንደማስያዣነት በመጠቀም ነው ያሉ አካላትም ተሰምተዋል፡፡
እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ትንበያ ዩክሬን በ2026 እና 2027 137 ቢሊዮን ዩሮ ያስፈልጋታል፡፡//

