የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የትራንስፖርት ታሪፍ ከተሻሻለበት ጊዜ ጀምሮ 357 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች ከትራንስፖርት እጥረት ባለፈ ከተቀመጠው ታሪፍ በላይ እያስከፈሏቸው መሆኑን ቅሬታቸውን በተደጋጋሚ ለአሐዱ አሰምተዋል፡፡

አሐዱም የነዋሪዎችን ቅሬታ አዳምጦ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ሰንዝሯል፡፡

በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን የትራንስፖርት ስምሪትና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ዬሴፍ ተስፋዬ ችግሮች መኖራቸውን አምነው ይህንንም ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የትራንስፖርት ታሪፍ ከተሻሻለበት ጊዜ ጀምሮ ትርፍ ለማግኘት ወይም ያለ አግባብ ጥቅም ለማግኘት ከመስመር ውጭ የትራንስፖርት አገልግሉት ሲሰጡ የነበሩ፤ ከታሪፍ በላይ የጫኑና ሌሎችን ጨምሮ 357 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሩ ጠቁመው ያለአግባብ ትርፍ ለማግኘት ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉና ከመስመር ውጭ የሚሰሩትን ኅብረተሰቡ ታርጋቸውን በመያዝ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበራቸው አሳስበዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe