የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ 22 ተሸከርካሪዎችን እና 33 ተጠርጣሪዎችን መያዙን አሳወቀ፤

ኮሚሽኑ በጥናት ላይ ተመስርቼ አደረኩት ባለው ኦፕሬሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችን እና 33 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየተስተዋለ ያለውን የተሽከርካሪ ስርቆት ለመከላከል እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ህግ ፊት ለማቅረብ የአዲስ አበባ ፖሊስ በጥናት ላይ በመመስረት የምርመራ እና የክትትል ቡድን አቋቁሞ ባካሄደው ኦፕሬሽን ነው ተሸከርካሪዎቹና ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት፤

በኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ እንደገለፁት ተሽከርካሪዎቹ እየተሰረቁ አብዛኞቹ ወደ ሃዋሳ ከተማ እንደሚወሰዱ በምርመራ ማረጋገጥ ተችሏል፤

ከተሰረቁት ተሽከርካሪዎች መካከል ሰባቱ በአዲስ አበባ የተገኙ ሲሆን የተቀሩት 15 ተሽከርካሪዎች ደግሞ በሀዋሳ ከተማ እና ከሀዋሳ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ተይዘው ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ተሽከርካሪ በመስረቅ ፣ የተሰረቀውን ተሽከርካሪ በመግዛት እና በመደለል ተሳትፎ ያደረጉ ከአዲስ አበባ 19 ከሃዋሳ ደግሞ 14 በአጠቃላይ 33 ግለሰቦችም ተይዘው ምርመራው በስፋት መቀጠሉን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹን ለጥበቃ ምቹ በሆነ ቦታ ባለማቆም በሚፈጠር ክፍተት እና አሽከርካሪዎች ለልዩ ልዩ ጉዳይ የመኪናቸውን ቁልፍ ተሽከርካሪ ላይ ጥለው ሲወርዱ እንዲሁም የተሽከርካሪውን ቁልፍ በልዩ ልዩ አጋጣሚ በማስቀረፅ ወንጀል ፈፃሚዎቹ የስርቆት ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደነበር በምርመራ መረጋገጡን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe