የአጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ከ156 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ

እኤአ 1868 በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰደው የአጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ከ156 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።
የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ)፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ የአርበኞች የልጅ ልጆች፣ በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።
ጋሻውን ለማስመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀ ጥረት ተደርጓል።
ከአንድ ዓመት በፊት ቅርሱ በእንግሊዝ ለጨረታ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም በተደረገው ጥረት ጨረታው እንዲነሳ ተደርጓል።
ልዑል ኤርሜያስ ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴና በኢትዮጵያ ንጉሳዊ በጎ አድራጎት ባለአደራ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe