የአፍሪካ ህብረት ቀን በኢትዮጽያ ብሔራዊ በዓል ተደርጎ እንዲከበር ተጠየቀ

ቀዳማዊ ሃይለስላሴ፡ጆሞ ኬኒያታ እንዲሁም ሴኮቱሬን ጨምሮ በሌሎች የወቅቱ መሪዎች የተወለደው የዛሬው የአፍሪካ ህብረት ቀን በኢትዮጽያ ብሔራዊ በዓል ተደርጎ እንዲከበር ተጠየቀ፡፡

የቀድሞው የአፍሪ አንድነት ድርጅት፡የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ምስረታ በዓል በኢትዮጽያ ብሔራዊ በዓል ተደርጎ እንዲከበር ጥያቄ መቅረቡ ተሰምቷል፡፡

ከ62 ዓመታት በፊት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በሚል የተቋቋመው የዛሬው የአፍሪካ ህብረት የምስረታውን ቀን በየዓመቱ ግንቦት 16 ያከብራል፡፡ታዲያ ይህ የምስረታ ቀን በኢትዮጽያ ብሔራዊ በዓል ተደርጎ እንዲቆጠር የሚጠይቅ ጥያቄ መቅረብ ቢጀምርም እስካሁን ምላሽ አልተሰጠውም ተብሏል፡፡

አፍሪካ ዴይ ኢንሼቲቪ የተባለ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ይህን ጥያቄ ከ2 ዓመት በፊት ለመንግስት ያቀረብኩ ቢሆንም እስካሁን ምላሽ አላገኘሁም ሲል ገልጻል፡፡ ምላሽ እስኪሰጠውም ጥያቄ ማቅረቡን እንደሚገፋበት ነው ያስታወቀው፡፡ የአፍሪካን ቀን ዙምባቡዌ፡ናሚቢያ፡ዛምቢያ፡ጋምቢያ፡ሞሪታኒያን ጨምሮ 7 ሀገራት በየዓመቱ ሜይ 25 ብሔራዊ በዓል አድርገው ያከብሩታል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe