የኢትዮጵያውያን የጥበብ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ያዘጋጀው የጥበብ ምሽት ሀምሌ 4 ቀን 2016 በአትላንታ በማሪዮት ሆቴል ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ተካሂዷል።
ጁላይ 4 የነፃነት ቀናቸውን አሜሪካውያን እያከበሩ ባሉበት ዋዜማ የአትላንታ የምሽት ሰማይ በርችት እየተንቦገቦገ ነው። ኮሜዲያን መስከረም ዘመኑን የዋጀ ቀልድ ቀልዷል።መጋቢ አዲስ እሸቱ አለማየሁ እንደወትሮው ልብ ሰርሳሪ ዲስኩር አሰምተዋል። ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታና ደራሲ ውድአላት ገዳሙ ከየመጽሐፎቻቸው ቅንጭብ ታሪኮችንና ግጥሞችን አንብበዋል። አርቲስት ትዕግስት ግርማ አንጎራጉራለች። የደራሲ አበባየሁ ታደሰ ድራማና ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት መነባነብ በመድረክ ቀርቧል።
በፕሮግራሙ መክፈቻ ስነ ስርአት ላይ የኢትዮጵያውያን የጥበብ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ ሰብሳቢ ቴዎድሮስ ታደሰ እንደገጸው ከስፖርት ውድድሩ ጋር በተያያዘ ወደከተማችን ለመጡ እንግዶች ልዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅት የማቅረብ ልምድ ያለን በመሆኑ ከስፖርት ፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን በመግለጽ ፕሮግራሙ አዝናኝ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብላል፡፡
ጋዜጠኛ ታምራት ሀይሉ “ ከዜሮ አመት የስራ ልምድና ሌሎች ወጎች መጽሐፍ ላይ ቅንጭብ ታሪኮችን አንብቦ የጋዜጠኝነት ሙያ ልዩ ገጠመኙን በግርጌ ማስታወሻ አጋርተል። በቅድመ ህትመት ግዢው ለተሳተፉ ሰዎች መጽሐፉንም አስረክባል። በመጨረሻም ለኢትዮጵያውያን የጥበብ ማህበረሰብ በሰሜን አሜሪካ አዘጋጆች የመጽሐፍ ስጦታ አበርክቶ ፕሮግራሙ ተፈፅሟል።

