የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኤርትራ ከትኬት ሽያጭ የሰበሰበ ገንዘብ ለማስመለስ በፍርድ ቤት የመሰረተው ክስ ውድቅ መደረጉን አሰታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ፣ ሞዛምቢክ እና ሩሲያ የሰበሰበውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ማውጣት እንዳልቻለ አስታወቀ
 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተጓዥ ደንበኞች ትኬት ሽያጭ የተሰበሰበ “ከፍተኛ መጠን” ያለው ገንዘብ ከኤርትራ፣ ሞዛምቢክ እና ሩሲያ ማውጣት እንዳልቻ ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታቋል፡፡
ተቋሙ ‹‹ከፍተኛ መጠን›› ሲል የገለጸውን ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ ከትኬት ሽያጭ የሰበሰበ ገንዘብ ለማስመለስ በኤርትራ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ እንደነበር ገልጾ በፖለቲካዊ ምክንያት አለመሳካቱን ገልጾአል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመትን ሪፖርት ባቀረቡበት መድረክ፣ አየር መንገዱ ከትኬት ሽያጭ የሰበሰበውን እና በኤርትራ ባንኮች የሚገኘውን ገንዘብ ለማውጣት እንቅፋት እንደገጠመው ተናግረዋል።
በተጨማሪም አየር መንገዱ በሞዛምቢክ እና በሩሲያ መጠኑ ያልተገለጸ ‹‹ከፍተኛ›› ገንዘብ እንዳለውና ይህንንም ለማውጣት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
‹‹በሞዛምቢክ እና በሩሲያ ከባድ ፈተና ገጥሞናል›› ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው በሞዛምቢክ በኩል ማስተካከያ በማድረግ የተጠራቀመውን ገንዘብ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
‹‹ሩሲያም የተጠራቀመ በጣም ብዙ ገንዘብ አለ አማራጭ መንገድ ፈልገን ለማውጣት እየሞከርን ነው›› ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2018 በጀት ዓመት አየር መንገዱ በዓመቱ 20.7 ሚሊየን መንገደኞችን ያጓጓዘ ሲሆን 897 ሺህ ቶን የካርጎ ጭነት እንዳጓጓዘ ገልጾአል።
በተጨማሪም 9 አዳዲስ አውሮፕላኖችን በግዢ እና በኪራይ ወደ ስራ በማስገባት ዓለም አቀፍ መዳረሻዎቹን 150 ሲያደርስ፣ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎቹን ወደ 25 ከፍ ማድረጉን ገልጾአል።
አየር መንገዱ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 9.1 ቢሊየን ዶላር ወይም ከ1.4 ትሪሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ ሲገለጽ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የተቋሙ ዓመታዊ ወጪ በ25 በመቶ ማደጉ ተነግሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe