ልማት ባንክ ለዘመናት ሲሰራበት የነበረውን የችርቻሮ ብድር አቅራቢነት የቢዝነስ ሞዴል በመቀየር ወደ ጅምላ ብድር አቅራቢነት ለመሸጋገር የሚያስችለውን የአምስት ዓመት ዕቅድ ማዘጋጀቱ ተሰምቷል፡፡
ለዓምስት ዓመት እንዲያገለግል ታስቦ የተዘጋጀው ፕላን እስከ ህዳር 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ ጸደቆ ወደ ስራ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
ባንኩ ከዚህ ቀደም መንግስት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የልማት ዘርፎች ለተሰማሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች የችርቻሮ ብድር አቅራቢ ሆኖ መዝለቁ ይነገራል፡፡
በቀጣይ በሚተገበረው አዲስ የቢዝነስ ሞዴል ግን ባንኩን ከችርቻሮ ብድር አቅራቢነት ወደ ጅምላ ብድር አቅራቢነት ያሸጋግረዋል፡፡
የጅምላ ብድር ማለት ብድርን ለግለሰብ ወይም በንግድና ኢንቨስትመንት ለተሰማራ ነጠላ ድርጅት ከማቅረብ በመውጣት የረጅምና የመካከለኛ ጊዜ ጥቅል ብድሮችን ለባንኮችና ለማይክሮ ፋይናስ ተቋማት ወደ ማቅረብ መሸጋገር ማለት እንደሆነ ይነገራል፡፡
የጅምላ ብድሩ የሚቀርብለት የንገድ ባንክ እንዲሁም የማይክሮ ፋይናስ ብድሩን ለታለመለት ዓላማ ማዋላቸውን በልማት ባንክ በኩል ክትትል እንደሚደረግለትም ተሰምቷል፡፡
የኢትዮጽያ ልማት ባንክ ለዚህ ዓላማ የሚያውለውን ሃብት ቦንድ በመሸጥ፡በኢትዮጽያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ በመሳተፍ ፡ከተመላሽ ብድር፡ከውጭ አበዳሪዎች እንዲሁም በመንግስት ከሚመደብ በጀት እንደሚያሰባስብ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡//

