የእስራኤል መከላከያ አሜሪካ ለሳውዲ ኤፍ 35 ተዋጊ ጄቶችን ለመሸጥ የያዘችውን እቅድ ተቃወመ

የእስራኤል ጦር ይህ ውሳኔ እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ያላትን የአየር የበላይነት የሚፈታተን ነው ብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሳውዲ አረቢያ ፍቅር እንዳላቸው ይታመናል፡፡ በመጀመሪያው ዙር የስልጣን ዘመናቸውም የውጭ ሀገር ጉዟቸው የነበረው ወደ ሳውዲ ነው፡፡ ዘንድሮም ዳግም ወደ ዋይት ሐውስ ሲመለሱ የመጀመሪያ ጉዟቸው ለደን ወይንም ካናዳ ሳይሆን ሳውዲ ነበር የሆነችው፡፡

የሳውዲው ንጉስ መሐመድ ቢን ሳልማን የትላንትናው የዋይት ሐውሱ ጉዟቸው ከ2018 ወዲህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡

በዚያን ዓመት ደግሞ የሳውዲው ጋዜጠኛ በቱርክ የሳውዲ ኤምባሲ መገደሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ጋዜጠኛው እንዲገደልም የሳውዲ መንገስት አዟል በሚል ሁሉም የምዕራብ ሀገራት ሳውዲን ሲገፉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን ያንን አላደረጉም ነበር፡፡ እንዲያውም ሲከላከሉላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

የትላንቱ የመሐመድ ቢን ሳልማን የጉዞ ዋነኛ አላማም ኤፍ 35 ተዋጊ ጄቶችን አሜሪካ እንድትሸጥላቸው ለማድረግ ነው፡፡ ትራምፕም ለወዳጃቸው ይህንን ለማድረግ ስለመወሰናቸው ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሳውዲ ኤፍ 35ን በጣም ፈልጋቸዋለች፤ከኢራንም ስጋት አለባት እናም እንሸጥላቸዋለን ብለዋል፡፡

ኤፍ 35 ተዋጊ ጄቶች እንደሌሎች አይነት ተዋጊ ጄቶች ሳይሆኑ የአሜሪካ እጅግ ዘመናዊ የጦር ተዋጊ ጄቶች ናቸው፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት እስራኤል እና ጥቂት የኔቶ አባል ሀገራት እነዚህ ተዋጊ ጄቶች አሏቸው፡፡ ሪያድ አሁን ከጥቂቶቹ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ነው እየጠየቀች ያለችው፡፡

ዋሽንግተን ምን አልባትም ይህን ውሳኔዋን ልትለውጠው እንደምትችል እየተሰማ ነው፡፡ ሳውዲ ከቻይና ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን አሜሪካ የኤፍ 35 ጄቶች ቴክኖሎጂን ሳወዲ ለቻይና ትሰጣለች የሚል ስጋት ሊያድርባት ይችላል ተብሏል፡፡

ሌላው ደግሞ የእስራኤል ጉዳይ ነው፡፡ እስራኤል አሁን በዚህ ስዓት 45 የሚሆኑ ኤፍ 35 ጄቶች በእጇ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሳውዲ ደግሞ ለግዢ የጠየቀችው 48 ጄቶችን ነው ይህም የምዕራብ ኤዥያን የሃይል ሚዛኑን ይለውጠዋል እንደ ማለት ነው፡፡

እናም በእነዚህ ሁለት ምክንያትቶች ሳውዲ ኤፍ 35 ጄቶችን ላይሸጥላት ይችላል እየተባለ ነው፡፡

የእስራኤል መከላከያም የአሜሪካን ኤፍ 35 ጄቶችን ለሳውዲ የመሸጥን እቅድ በይፋ እንደሚቃወም ገልጻል፡፡

ይህ የአሜሪካ ውሳኔ የእስራኤልን የአየር ሃይል የበላይነትን የሚያስነጥቅ ነው ብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህን ማድረግ የፈለጉት በሳውዲ እና በእስራኤል መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲሻሻል ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ነው፡፡

እስራኤል እና ሳውዲ በዚህ ወቅት ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዉ ግንኙነት የሌላቸው ሀገራት ናቸው፡፡

ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው አራት ሀገራት ከእስራኤል ጋር ግንኙነታቸውን እንዲያሻሽሉ አድርገዋል፡፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬት፡ባህሬን፡ሱዳን እና ሞሮኮ ናቸው፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe