በኢትዮጵያ በልብ ህክምና ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነዉን የልብ ህክምና ሆስፒታል ያቋቋሙት ካርዲዮሎጂስት ፍቅሩ ማሩ ባለፈዉ ዕሁድ ከዚህ አለም ድካም ማረፈቸዉንና በዛሬዉ ዕለት ቀብራቸዉ በስዊድን ሀገር መፈጸሙን በአዲስ የልብ ህክምና ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ ፍቅረማሪያም ነግረውናል፡፡
በሰለጠነዉ አለም ተምረዉ ወደ ትዉልድ ሀገራቸዉ በመምጣት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን የልብ ሆስፒታል በማቋቋም በልብ ህክምናዉ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ህዝባቸዉንና ሃገራቸዉ ያገለገለ ነበሩ።
የጥቁር አንበሳው የልብ ህሙማን ህክምና ማዕከል ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ጎንደር ዩኒቨርስቲና ሌሎቹም የልብ ህክምናን እንዲጀምሩ ካገዙት ውስጥ መሆናቸውን ዶ/ር ቴዎድሮስ ነግረውናል፡፡
በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሲዊድናዊ የሆኑት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ካለፈው አንድ አመት ወዲህ የጤናቸው ነገር ታውኮ በህክምና ላይ እንደነበሩ የነገሩን ዶ/ር ቴዎድሮስ ፍቅረማሪያም ከህልፊታቸው ከሳምንት በፊትም በአዲስ አበባ ተገኝተው የአዲስ የልብ ህክምና የማስፋፊያ ስራን መርቀው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

