የክልል መንግስታት በጀታቸውን ወደ ግል ባንክ ማዞራቸው በሙሉ አቅም እንዳልሰራ ምክንያት ሆኗል አለ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ

የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ አንዳንድ የክልል መንግስታት በጀታቸውን ወደ ግል ባንክ ማዞራቸው በሙሉ አቅም እንዳልሰራ ምክኒያት ሆኗል አለ፡፡

አንዳንድ የክልል መንግስታት በጀታቸውን ወደ ግል ባንኮች የማዞር ሁኔታ መቀጠሉና በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ ችግር የባንኩ ቅርንጫፎች በሙሉ አቅማቸው እንዳይሰሩ ማድረጉን የባንኩ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዜዳንቱ እንደገለጹት የባንክ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 2.998 ትሪሊየን ብር ደርሷል፤ከዚህ ውስጥም የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ 49.3 ፐርሰንት የገበያ ድርሻ በመያዝ ከፍተኛውን ድርሻ ይዟል፡፡

ባንኩ 367 ቢሊየን ብር ተጨማሪ ተቀማጭ መሰብሰቡብንና ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ344.4 ፐርሰንት እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ባንኩ ከሰጣቸው ብድሮች በመጀመሪያው 8 ወራት 149.26 ቢሊየን ብር መሰብሰቡብንና ካምናው ጋር ሲወዳደርም የ66.8 ፐርሰንት እድገት ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe