የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል በሚል ከሁለት አመት በፊት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተግባራዊ ከተደረጉ የገንዘብ ፖሊሲ እርምጃዎች አንዱ የባንኮች አመታዊ የብድር እድገት ላይ ገደብ መጣል ነበር፡፡
ሆኖም ከወለድ ነፃ ሆነው የተመሰረቱትን ጨምሮ አዳዲሶቹ ባንኮች ገና አቅም አላበጀንም በማለት የማእከላዊ ባንኩን ውሳኔ ሲቃወሙ ነበር፡፡
ብሄራዊ ባንክ የወለድ እደገት መቶኛውን ሁለቴ ያሻሻለ ቢሆንም ባለፈው መስከረም ወር ሙሉ ለሙሉ አነሳለው ያለውን እቅድ ግን ተግባራዊ ሳያደርግ ቀርቷል፡፡
ከሰሞኑ እንደተሰማው ደግሞ በአራቱ የወለድ ነፃ ባንኮች፣ ዘምዘም፣ ሂጅራ፣ ራሚስ እና ሸበሌ ባንኮች ላይ ይህ የብድር እድገት ገደብ ተፈጻሚ መሆኑ እንዲቀር ብሄራዊ ባንክ ወስኗል፡፡
ባለሞያዎች እንደሚሉት እነዚህ ባንኮች ወለድ የማይቀበሉ በመሆኑ ከብድር የሚተርፋቸውን ከህዝብ የሰበሰቡትን ገንዘብ እንደ ቦንድ እና የግምጃ ቤት ሰነድ ወደ መሰሉ የወለድ ገቢ በሚያስገኙ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ባለመቻላቸው ለጉዳት ሲዳረጉ ቆይተው ነበር፡፡
በመሆኑም ከተደጋጋሚ ውትወታ በኋላ ብሄራዊ ባንክ ለአራቱ ባንኮች ብቻ ገደቡን አንስቷል፡፡
ለባንኮቹ የብድር ጣራ መነሳት እየወረደ ላለው የዋጋ ግሽበት ጫና አይፈጥርም ወይ ለሚለው ጥያቄ ያን ያህል ተጽእኖ የሚያሳድር አለመሆኑን የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ፍቃዱ ድጋፌ ለፎርቹን መናገራው ነው የተጠቀሰው፡፡#ቅዳሜገበያ
የወለድ ነፃ ባንኮች ከብድር እድገት ገደብ ነጻ ሆኑ

