የዓለማችን ድሃው ፕሬዚዳንት የሚል መጠሪያን ይዘው የነበሩት የቀድሞው የኡራጓይ ፕሬዜዳንት በ89 ዓመታቸው አረፉ፡፡
ፕሬዜዳንት ጆሴ ሙሂጋ የላቲን አሜሪካዋን ኡራጓይ ከ2010 እስከ 2015 ድረስ በፕሬዜዳንትነት መርተዋል፡፡ ፕሬዜዳንት ሙሂጋ ይከተሉት በነበረው ቀለል ያለ የህይወት ምርጫ በብዙዎች ዘንድ ትኩረት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል፡፡
ከፕሬዜዳንትነት ስልጣናቸው ሲነሱ ቀድሞ ይኖሩበት ወደ ነበረው የገጠር ቤታቻው ተመልሰው እስከ ህልፈታቸው ድረስ በዚያ ኖረዋል፡፡የሌሎች ሀገራት መሪዎች እንደሚያደርጉት የተቀናጣ ኑሮ እንዳልነበራቸው በስፋት ይነገርላቸዋል፡፡
መኪናቸውም ጥይት የማይበሳው ዘመናዊ መኪና ሳይሆን፤የ1987 ስሪት የሆነች ቮልስ ቫገን ነበረች፡፡ፕሬዜዳንቱ በሚያሳዩት ትሁት ባህሪ የተነሳም በሀገሬው ሰዎች ፔፔ የሚል የሚል ተቀጽላ ስም ነው የሚጠሩት፡፡
ፕሬዜዳንት ሞሂጋ ከጉሬላ ተዋጊነት እስከ ፕሬዜዳንትነት የደረሱም ናቸው፡፡ በትግል ዘመናቸውም ለ13 ዓመታት ያህል በእስር አሳልፈዋል፡፡ለህልፈታቸው ምክኒያት የሆነው ነገር በግልጽ ባይነገርም በካንሰር በሽታ ሲሰቃዩ እንደነበር ታውቋል፡፡ የላቲን አሜሪካዋ ኡራጓይ ፕሬዜዳንት ጆሲ ሞሂጋ ከ2010 እስከ 2015 በፕሬዜዳንትነት የመሩት ሞሂዳ የደመወዛቸውን 90 ከመቶ የሚሆነውን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይሰጡ እንደነበርም ይነገርላቸዋል፡፡
በርግጥ ፕሬዜዳንቱ ለችግሮች መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ስለ ችግሮቹ ለህዝቡ መልሰው ማውራት መውደዳቸው ደካማ ጎን ተብሎ የሚነሳባቸው ሲሆን፤በተጨማሪም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በህግ በመፍቀዳቸውም ትችት ይቀርብባቸዋል፡፡

