የዛሬ 62 አመት ሀገራችን ባነሳችው የአፍሪካ ዋንጫ ከነመንግስቱ ወርቁ ጋር የብሄራዊ ቡድኑ አባል የነበሩት ባሻ ኃይሉ አበበ ጥር 29 ቀን 2016 ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።
ባሻ ኃይሉ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ዋንጫ ከመወከል በ3ኛ በ6ኛውና በ10ኛው የአፍሪካ ዋንቻ ላይ በተከላካይ መስመር ላይ የተሰለፉና የተጫወቱ ሲሆን 3ኛው የአፍሪካ ዋንጫን ካነሳው የእነመንግስቱ ወርቁ ቡድን አባል ነበሩ፤ ባሻ ሃይሉ ከዚህ በተጨማሪ አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ ባሸነፈበት በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ማራቶን ሲያሸንፍ በ100 እና በ3ሺ ሜትር ሀገራችንን የወከሉ አትሌት ነበሩ፤ ይህም በአፍሪካ ዋንጫና በኦሎምፒክ የተሳተፉ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ያደርጋቸዋል።
ባሻ ኃይሉ 1970 አእና 1980ዎቹ የተለያዩ የእግር ካስ ክለቦችን ያሰለጠኑ ሲሆን ሜታና ህንጻ ኮንስትራክሽንን የመሳሰሉ ታዋቂ ክለቦችን ያሰለጡኑ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች በአንድ ወቅት ለዋንጫ ሲደርሱ የትኛውን ክለብ ይዘው ወደሜዳ መገባት እንዳለባቸው በመቸገራቸው ቡድኖቹ ያለአሰልጣኝ የዋንጫ ጨዋታውን እንዲጫወቱ ማድረጋቸውና ሜታ ዋንጫ ማንሳቱን በወቅቱ ለገነነ ሊብሮ እንደገለጹለት ይታወሳል፡፡
ባሻ ሃይሉ ሶሰት ሴትና አንድ ወንድ ልጆችን ያፈሩ ሲሆን ወንድ ልጃቸው ደረጄ ኃይሉ /ባቢ/የሳቸውን ፈለግ በመከተል የቀድሞው የኢትዮጵያ ወጣትና ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች መሆን ችላል፡፡ የባሻ ሃይሉ አበበን አስተዋጽሾ ከግምት በማስገባት የሰሜን አሜሪካ የግር ካስ ፌዴሬሽን በ2008 የክብር እንግዳ አድርጎ አሜሪካ ጋብዛቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡
የባሻ ሃይሉ አበበ የቀብር ስነ ስርዓታቸው በማግስቱ ጥር 30 ቀን 2016 በየካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈፀማል።

