የዩጋንዳ ጦር አዛዥ እስራኤልን ለመከላከል 100ሺ ሰራዊት እናሰማራለን አሉ

የዩጋንዳ ጦር አዛዥ እና የፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ልጅ ጀነራል ሙሁዚ የክርስቶስ ሀገር የሆነችውን ቅድስት ሀገር እስራኤልን ለመከላከል ይህንን እናደርጋለን ሲሉ በኤክስ ገጻቸው ማጋራታቸው መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ምንም እንኳን ጀነራሉ ይህን ይበሉ እንጂ ዩጋንዳ በዚህ ስዓት ያላት አክቲቭ ወታደር ከ50ሺ በታች ነው፡፡ ተጠባባቂ ወታደሮች ደግሞ 10ሺ ገደማ እንደሆኑ ሪፖርቶች ያመላክታሉ፡፡

የዩጋንዳ ጦር አዛዥ እና የፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ልጅ ጀነራል ሙሁዚ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ቆንጆ ሴት ለትዳር እንዲልኩላቸው ጠይቀዋልም ተብሏል፡፡

ጀነራል ሙሁዚ ካይኔሩካጋባ ቅዳሜ እለት በኤክስ ገጻቸው ባጋሩት ጹሑፍ ከቱርኪዬ 1 ቢሊዮን ዶላር እና በጣም ቆንጆ ሴት እንደሚፈልጉ ጽፈዋል፡፡ አንካራ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ እንድትሰጥም የ30 ቀናት ጊዜ ሰጥቻለሁ ብለዋል፡፡ ቱርኪዬ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለጥያቂያችን ምላሽ ካልሰጠች ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሙሉ ለማቋረጥ እንገደዳለን ብለዋል፡፡

ጀነራል ሙሁዚ ከዚህ ቀደም በ2022 የጣሊያኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒን ለማግባት በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁም ከብቶችን ጥሎሽ እንደሚሰጡ ጽፈው መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡ ጠየቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ይህንን ጥያቄ ውድቅ የሚያደርጉ ከሆነ ሮምን ለመያዝ እንገደዳለን ብለው ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ጎረቤት ሀገር የሆነችውን ናይሮቢ ኬኒያን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የመያዝ አቅም አለን ብለው በርካታ ኬኒያዊያንን አስቆጥተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አባታቸው ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ለዚህ ለልጃቸው ንግግር ይፋዊ ይቅርታ መጠየቃቸውም እንዲሁ ይታወሳል፡፡

ጀነራሉ ከዚህ ባለፈ እስራኤልን ለመከላክ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዩጋንዳዊያንን ወታደሮች እንደሚያሰልፉም በይፋ ተናግረዋል፡፡ ዩጋንዳ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ላለው ተልዕኮ በርካታ ወታደሮችን በማዋጣት ከ2007 ጀምሮ ንቁ ተሳታፊ ሀገር ናት፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe