የጀርመን እና የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የጀርመን ፌደራል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ እና የፈረንሳይ አቻቸው ካትሪን ኮሎና በመጪው ሳምንት ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አብረው እንደሚጓዙ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።
የጉዞው ዓላማ ባለፈው ህዳር ወር በህወሓት እና በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት እንዲጠናከር አስተዋፅኦ ለማበርከት መሆኑም ተገልጿል።
እንደ ፈረንሣይ ዲፕሎማቶች የቤርቦክ እና የኮሎና ጉዞ በመጭው ሳምንት ሐሙስ እና አርብ ቀን ተቆርጦለታል። ሚኒስትሮቹ በእርዳታ አቅርቦት፣በኢትዮጵያ፣ በአውሮፓ ህብረት እና በአፍሪካ ህብረት ግንኙነት ላይ እንደሚመክሩም ዘገባው አመልክቷል።
የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የጋራ ጉዞ የፍራንኮ-ጀርመን ወዳጅነት መሠረት የሆነውን የኤሊሴ ውል 60ኛ ዓመት ከመከበሩ ጥቂት ቀደም ብሎ መሆኑ፤የጠንካራ የፍራንኮ-ጀርመን ግንኙነት ምልክት መሆኑን ኮሎና ገልፀዋል ሲል የዘገበው የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe