የጋናው ፕሬዘዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ባለስልጣናት እስከ እሮብ፣ ሜይ 7፣ 2025 ንብረታቸውን ካላስመዘገቡ ራሳቸውን ከስራ እንዳባረሩ ይቁጠሩት ሲሉ ተናገሩ
ፕሬዘዳንት መሃማ ይህንን ያሉት የተሿሚዎችን የስነ ምግባር ደንብ ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው
የጋናው ፕረዚደንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ለሁሉም የፖለቲካ ተሿሚዎች ሁሉን አቀፍ የስነምግባር ህግ አውጥተዋል፣ ይህም ለተሻለ ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና ስነምግባር የተወሰደ እርምጃ ነው ተብሏል።
የስነ ምግባር ደንቡ ፕሬዝዳንቱን፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱን፣ ሚኒስትሮችን እና ምክትል ሚኒስትሮችን እና የፕሬዝዳንት ሰራተኞችን ጨምሮ የስራ አስፈፃሚ አካላትን ባለስልጣናት ሁሉ ይመለከታል።
ገለልተኝነትን ለማስጠበቅ እና ተገቢ ያልሆነ ተጽእኖን ለመከላከል ህጉ ተሿሚዎች ስጦታዎችን ወይም ውለታዎችን በተለይም የመንግስት ውሳኔዎች ላይ ፍላጎት ካላቸው ግለሰቦች ወይም ኩባንያዎች እንዳይቀበሉ ይከለክላል።
ከ GH¢20,000.00( የጋና ገንዘብ ) በላይ በሆነ ኦፊሴላዊ ተሳትፎ ወቅት የተቀበሉት ስጦታዎች ፕሬዝዳንቱ ካልፈቀዱ በስተቀር ከቢሮ ሲወጡ ስራ ሲያቆሙመሰጠት አለባቸው።
የመንግስት ገንዘብን በመጠቀም ሰራተኛን በመጠኑ ለማበረታታት ካልሆነ በቀር አላስፈላጊ ቁሳቁስ መግዛት እና መስጠት በአጠቃላይ ክልክል ነው፣
በሚኒስትሮች የሚደረጉ ሁሉም ይፋዊ ሆነ እና መደበኛ ያልሆኑ አለም አቀፍ ጉዞዎች ጭምር የሰራተኞች ፅህፈት ቤት ሳያውቅ መጏዝ አይችሉም
እስከ ማርች 31 ቀን 2025 የተሾሙ ተሿሚዎች የግል ንብረታቸውን ካላስመዘገቡ የሶስት ወራት ደሞዛቸውን እንደሚቀጡ እና ለጋና የህክምና ትረስት ፈንድ ብሩ ይሰጣል ብለዋል
ሆኖም እስከ እሮብ፣ ሜይ 7፣ 2025 መገባደጃ ማንኛችሁም ባለስልጣን ንብረቶቻችሁን የማያሳውቁ ከሆነ ራሳችሁን በራሳችሁ ከስራ እንዳቋረጣችሁ እወቁት ብለዋል
ይህን ህግ በጥብቅ መከተል በፖለቲካ ልሂቃን ላይ እምነትን ይመልሳል ዲሞክራሲያችንን ለማጠናከር ይረዳል በዲሲፕሊን እና በትህትና ለጋና ህዝብ በማይቋረጥ ቁርጠኝነት መንገድ እንጓዝ ሲሉ ፕሬዝዳንት ማሃማ አጠቃለዋል።
የጋና ባለስልጣናት እስከ እሮብ ድረስ ንብረታቸውን ካላስመዘገቡ ከስራ ይባረራሉ ተባለ
SourceWazema

