የግል አየር መንገዶች በዓለም አቀፍ በረራ አገልግሎት እንዲሰማሩ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡ ይህን የሚፈቅድ የፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ መታሰቡን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ከሲቪል አቬሽን ባለስልጣንና በአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት ከተሰማሩ የግል አየር መንገዶች ጋር ትላንት ውይይት ማድረጋቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
በዚህ ውይይት ወቅትም የግል አየር መንገዶች ከአገር ውስጥ ገበያ ከሚገኝ ገቢ አውሮፕላን ለመግዛት፡ለመከራየትና የመለዋወጫ ዕቃዎችን ለመግዛት በቂ ባለመሆኑ ዓለም አቀፍ በረራ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጽያ አየር መንገድ እንኳን በከሰረበት የአገር ውስጥ በረራ እኛ ትርፋማ ልንሆን እንደማችል ይታወቃል ብለዋል የግል አየር መንገዶች፡፡
ራሱን የቻለ የኤርፖርት አስተዳደር ችሎት እንዲቋቋም፡የገቢዎችና ጉምሩክ አሠራር እንዲሻሻልና በዓለም አቀፍ በረራ እንዲሰማሩ እንዲደረግ ጠይቀዋል ተብሏል፡፡
የኢትዮጽያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን ለኢትዮጽያ አየር መንገድ ብቻ የተፈቀዱት ዓለም አቀፍ በረራዎች ከአሠራር፡ከቀጠናዊ ትስስርና ከአገራዊ ገጽታ አኳያ የነበረውን ፖሊሲ የማሻሻልና ስትራቴጂውን የማላላት እቅድ እንዳለ መግለጹ ተነግሯል፡፡
በተመሳሳይ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎችን ለአገር ውስጥ የግል አየር መንገዶችም ለመክፈት የፖሊሲ ማሻሻያዎች ለማድረግ መታሰቡን ገልጻል፡፡
መንግስት ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተጨማሪ እንደ ባህርዳር፡መቀሌና ድሬዳዋ ባሉ አውሮፕላን ማረፊያዎች ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለመጀመር ካሰበው እቅድ ጋር የግል አየር መንገዶች በዚሁ መንገድ ለማሳተፍ ታቅዷል ተብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ የኦፕሬተርነት ፈቃድ ወስደው በሙሉ አቅም የማይሰሩ አካላትን ወይ በሙሉ አቅማችሁ ስራ አልያም ከዘርፉ ውጡ ሲልም አስጠንቅቋል፡፡//

