የቲያንስ ተከሳሾች ተቀጡ፡፡ለዓመታት ሲያካሂዱት በነበረው ሕገ-ወጥ የ“ፒራሚድ” የሽያጭ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት የቲያንስ ኢትዮጵያ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እና አመራሮቹ ላይ የ17 ዓመት ጽኑ እስራትና የ40 ሚሊዬን ብር ቅጣት ተወሰነባቸው
ለዓመታት ሲያካሂዱት በነበረው ሕገ-ወጥ የ“ፒራሚድ” የሽያጭ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት የቲያንስ ኢትዮጵያ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር እና አመራሮቹ ላይ የ17 ዓመት ጽኑ እስራትና የ40 ሚሊዬን ብር ቅጣት ተወስኖባቸዋል።
ድርጅቱ የአልሚ ምግብ አስመጪነት ፈቃድን ሽፋን በማድረግ፣ ከ2004 እስከ 2008 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ለግል ጥቅም በማዋልና የሸማቾችን መብት በመጣስ በዓቃቤ ሕግ ክስ እንደቀረበበት መረጃው ያስረዳል።
ተከሳሾቹ ግለሰቦችን በ”ኮሚሽን ሽያጭ ወኪል” ስም በመመልመል፣ አዳዲስ ሰዎችን ወደ ሰንሰለቱ ሲያስገቡ የመኪና ሽልማት፣የውጭ ሀገር ጉዞና ከፍተኛ የገንዘብ ጉርሻ እንደሚያገኙ በማታለል ሀሰተኛ ገለጻ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ይህ ተግባር በንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ እንዲሁም በወንጀል ሕግ የተከለከለ የፒራሚድ ሽያጭ ሆኖ በመገኘቱ፣ ድርጅቱ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀልም ጭምር የፍርድ ውሳኔ ተላልፎበታል።
በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ 1ኛ ተከሳሽ ቲያንስ ኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን ብር እንዲቀጣ ሲወስን፣ አመራሮቹ ሚስተር ዶዮንግ ጋንግ እና አቶ ቴዎድሮስ በቀለ እያንዳንዳቸው በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ10 ሚሊዮን ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
(ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)
የ“ፒራሚድ” የሽያጭ ሲያካሂዱ የተገኙት የቲያንስ ኢትዮጵያ ተከሳሾች የ17 ዓመት ጽኑ እስራትና የ40 ሚሊዬን ብር ቅጣት ተወሰነባቸው

