የ2026 የሚስ ወርልድ አፍሪካ ውድድር፡ የደቡብ አፍሪካ ተወካይ ሮማንዳ ሆምቢር አሸነፈች
የሚስ ወርልድ ደቡብ አፍሪካ፣ ሮማንዳ ሆምቢር፣ በ2026 የሚስ ወርልድ አፍሪካ የHead-to-Head ውድድር አሸናፊ ሆና ወደ ሚስ ወርልድ ምርጥ 40 ቀጥተኛ መግቢያ አገኘች።
ደቡብ አፍሪካዋ የውበት ንግስት የናይጄሪያዋን ሶዬ ካሪቢ ጆርጅ፣ የኬንያዋን ትሪዛህ ሙሄንጄ አካላ፣ የዛምቢያዋን ዶ/ር አዳህ ሙሺቢ እና የኤርትራዋን ስህን ሃብትአብ ተወልደመድንን ያካተተውን ውድድር የአህጉሪቱ ምርጥ 5 አሸንፋለች።
የሆምቢር የድል ዜና መድረከ ላይ ባደረገቸው ስሜታዊ ንግግሯ የታወቀ ሲሆን፣ በውስጡም ስለጤና ጉዞዋ በመናደር፣ ልብ የሚነኩ ልምዶቿን አካፍላለች። “ስለጤና ችግሮቼ መናገር በጣም ከባድ ነበር፣ ምክንያቱም መታመም ብዙ እፍረትን ያስከትላል፣ በተለይም ሴቶችን እንደ ደካማ አድርጎ በሚመለከት ማህበረሰብ ውስጥ“ በማለት በስሜት ተናግራለች።
ግልጽ ያደረገቻቸው ትዝታዎቿ የአህጉሪቱ ድል እንድታገኝ ከማድረግ ባሻገር፣ ስለ ተጋላጭነት፣ ጽናት እና በሐቀኝነት ስለሚገኝ ጥንካሬ ምሳሌ ሆኖ ተሰምቷል።
በዚህ ምሽት በተካሄደው ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊቷ ሚስ ኢትዮጵያ ሩት ይርጋለም ከእህቷ አሰቃቂ ግድያ ማግስት ወደ ውድድሩ መሄዷንና በጥንካሬ ለታዳጊ ሴቶች ምሳሌ ለመሆን እንደምትጥር ብተትናገርም ወደ ተከታዩ ዙር ሳታልፍ ቀርታለች፡፡

