ዳሸን ባንክ ለደንበኞቹ የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ የሚፈፅሙበትን ዲጂታል የክፍያ አማራጭ አቀረበ

ዳሸን ባንክ ለደንበኞቹ የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ በዳሸን ሱፐር አፕ መፈፀም የሚችሉበትን አገልግሎት ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ይፋ አደረገ፡፡
ከዛሬ ጀምሮ የዳሸን ባንክ ደንበኞች በተመረጡ የነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ ሲቀዱ ክፍያቸውን በዳሸን ሱፐር አፕ በሶስት ክሊክ ብቻ መፈጸም የሚችሉበት አገልግሎት አቅርቧል፡፡ ይህም ደንበኞች አገልግሎቱን በቅፅበት እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው፡፡ በቅርቡም ዳሸን ባንክ ይህንን አገልግሎት በሁሉም ማደያዎች የሚጀምር ይሆናል፡፡
ነዳጅ የሚቀዱ የዳሸን ባንክ ደንበኞች የዳሸን ሱፐርአፕ መተግበሪያ ውስጥ በመግባት በሚኒ አፕ መተግበሪያ ውስጥ የሚገኘውን የነዳጅ ክፍያ (Fuel Payment) አማራጭ በመምረጥ የሚላክላቸውን የነዳጅ ክፍያ ኮድ በማስገባት ከፍያቸውን መፈፀም፤ አልያም በአማራጭነት የቀረበውን የኪው አር ኮድ ስካን በማድረግ በቀላሉ ክፍያቸውን ወዲያውኑ መፈፀም ይችላሉ፡፡
በዳሸን ሱፐርአፕ መተግበሪያ የቀረበው አገልግሎት ለአሽከርካሪዎች፣ ለነዳጅ ማደያዎችና ለነዳጅ ተቆጣጣሪ የመንግስት አካላት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተጀመረውን የነዳጅ ማደያዎች የገንዘብ አከፋፈል ስርዓት ወደ አስተማማኝና ዘመናዊ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት የሚቀይርና የፋይናንስ አካታችነትን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
ዳሸን ባንክ ከነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ጋር በተለያዩ ዘርፎች በጋራ የሚሰራም ሲሆን ለዚህም ባንኩ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ አዳዲስ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ ግንባር ቀደም የሆነው ዳሸን ባንክ፣ በቀጣይም ለደንበኞቹን አዳዲስ አገልግሎቶችን ያቀርባል፡፡
የነዳጅ ግብይቱን ለማዘመን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ያበለጸገዉን መተግበሪያ ከዳሸን ሱፐር አፕ ጋር በማጣጣም የነዳጅ ክፍያ መፈፅም እንዲያስችል ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡
(ዳሸን ባንክ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe