ዳሸን ባንክ በምርጥ 100 የአፍሪካ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ከዚህ ቀደም የነበረውን ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ አሻሻለ፡፡
የተለያዩ የባንኮች መመዘኛ መስፈርቶችን በመጠቀም በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ 100 ምርጥ የአፍሪካ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ የሚያደርገው የአፍሪካን ቢዝነስ ማጋዚን፣ ከሰሞኑ የ2025 ምርጥ ባንኮችን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ዳሸን ባንክም በዘንድሮው ዝርዝር አምና የነበረውን ደረጃ በከፍተኛ ቁጥር አሻሽሏል፡፡
እኤአ በ2024 ከአፍሪካ ምርጥ 100 ባንኮች ዝርዝር በ87ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የነበረው ዳሸን ባንክ እኤአ በ2025 16 ደረጃዎችን አሻሽሎ 71ኛ ላይ የተቀመጠ ሲሆን፣ ይህም በምርጥ 100 የአፍሪካ ባንክ ዝርዝር ውስጥ ከገቡት አራት የኢትዮጵያ የግል ባንኮች ውስጥ በሁለተኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አድርጎታል፡፡
ከምርጥ 100 የአፍሪካ ባንኮች ዝርዝር ውስጥ 21 የሚሆኑት በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ አገራት የተወጣጡ ባንኮች ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በድምሩ ስድስት የሚሆኑ ባንኮች በዚህ ዝርዝር ውስጥ ገብተዋል፡፡

