ባለፉት ዘጠኝ ወራት1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አግኝቷል፣ የኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ 30 ዓመታት የተጓዘው ዳሸን ባንክ፣ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገሩንና በ2018 ሒሳብ ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን አስታወቀ።
ባንኩ የ30ኛ ዓመት ምሥረታ ክብረ በዓሉ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ሐሙስ ሚያዝያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደበት ወቅት እንዳስታወቀው፣ ከምሥረታው ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ዕድገት እያስመዘገበ በመዝለቅን አጠቃላይ የሀብት መጠኑ በ2018 ዓ.ም. ዘጠነኛ ወር መጨረሻ ላይ ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኗል። ባንኩ በ2017 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ላይ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 255 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ በዘንድሮው ሒሳብ ዓመት ዘጠኝ ወራት የ55 ቢሊዮን ብር ጭማሪ በማሳየት ከ300 ቢሊዮን ብር ተሻግሯል። የባንኩ የሀብት መጠን ያሳየው ዕድገት ያለውን አቅም እንደሚያሳይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል፡፡ ከ30 ዓመት በፊት በ15 ሚሊዮን ብር ካፒታልና በአሥራ አንድ ባለአክሲዮኖች የተቋቋመው ዳሽን ባንክ፣ ዘንድሮ 30ኛ ዓመቱን በደፈነበት ወቅት አጠቃላይ ካፒታሉ 30 ቢሊዮን ብር፣ ባለአክሲዮኖቹ ደግሞ ከአራት ሺሕ በላይ ሆነዋል፡፡… (ሪፖርተር)

