የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በፍጥነት በሚዛመት የፕሮቴስት ካንሰር መጠቃታቸው በህክምና ባለሙያዎች ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው የ82 ዓመቱ ጆ ባይደን የተገኘባቸው የፕሮቴስት ካንሰር ወደ አጥንታቸው እየተስፋፋ እንደሚገኝ ገልጻል፡፡
ጆ ባይደን ባለፈው አርብ ባደረጉት ምርመራ ነው ካንሰር እንዳለባቸው የታወቀው፡፡ ህመማቸው ከፍተኛ ደረጃ በሚል እንደተለየም ተሰምቷል፡፡ ባይደን እና ቤተሰቦቻቸው የህክምና አማራጮችን እየፈተሹ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
ጆ ባይደን የመጀመሪያ ልጃቸውን በ2015 በሞት ያጡት በጭንቅላት ካንሰር ምክኒያት ነው፡፡/

