በአሜሪካ-እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ሳቢያ በዓለም ላይ የሚገኙ ሃያ (20) ግዙፍ አየር መንገዶች ጦርነቱ ከተጀመረበት የካቲት ወር ጀምሮ 53 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የገበያ ዋጋቸውን ማጣታቸውን ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።
ዘገባው የአየር መንገዶቹን ስም በዝርዝር ከማስቀመጥ ተቆጥቧል።
አየር መንገዶቹ ይህን ያህል ከፍተኛ ሀብት ሊያጡ የቻሉት ፦
– የነዳጅ ዋጋ በመናሩ፣
– የጸጥታ ስጋት ባለባቸው ቀጠናዎች በረራዎች በመሰረዛቸው፣
– የበረራ መስመሮች በመቀየራቸው ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።
ይህም በዓለም አቀፉ የአቪዬሽን ዘርፍ እና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መናጋት መፍጠሩ ተነግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

