ጎዶ ስማርት ሪል ስቴት በኢትዮጵያ የቤት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ለቤት ፈላጊዎች ታላቅ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ

በአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ አንዱ የሆነው ጎዶ ስማርት ሪል ስቴት የቤት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እና ዜጋውን የቤት ባለቤት ለማድረግ ብሎም የአካባቢውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማጎልበት እየሰራ ሲሆን የድርጅቱ ባለ ራዕይ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ደረጄ ማሙዬ እንደገለጹት ‘’ከዚህ በፊት ካሬ በ 75ሺ ብር ሲሸጥ የነበረው የኑሮ ንረትን ምክንያት በማደረግ እስከ ስኔ 30 የሚቆይ ታላቅ ቅናሽ በማድረግ ቤት በካሬ 67,500 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቀዋል።’’

የጎዶ ስማርት ሪል ስቴት ፕሮጀክት በግንባታ ላይ መሆኑ የሚታውቅ ሲሆን ግንባታው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በተለምዶው ሜዳ ጋራዥ ቴክለሀይማኖት አከባቢ በ10,000 ካሬ ሜትር (1 ሄክታር) መሬት ላይ ያረፈ ነው።  ሕንፃው እስከ 35 ወለል ያለው ሲሆን 4 ሕንፃዎችንና ከፍ ያሉ ማማዎችን አንድ ላይ በማቀናጀት ለተለያዩ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ዘመናዊ እንዲሁም ወጪ የማይጠይቁ ከ1 እስከ 4 መኝታ ክፍሎች ያሉት አፓርተማዎችን ያቀፈ ነው።

  • 1 መኝታ ቤት– 45 ካሬ ሜትር ፤ባለ 2 መኝታ ክፍሎች– 90 ካሬ ሜትር ፤ባለ 3 መኝታ ክፍሎች– 120 ካሬ ሜትር፤ባለ 4 መኝታ ክፍሎች– 150 ካሬ ሜትር በተጨማሪ የግንባታው ቦታ ከ10 እስከ 200 ካሬ ሜትር የሚለያዩ ዩኒቶች ያሉት አፍሪካን ቢዝነስ ሴንተር የተባለ የገበያ ማዕከል አካቷል። ይህም የአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴ በማበረታታት ለነዋሪዎቹ የዕለት ተዕለት ምቹ ሁኔታዎችን ለማቅረብ ያለመ ነው።

የዋጋ ቅናሹ 25% ለሚከፍሉ የቤት ፈላጊዎች እስከ ሰኔ 30፣ 2017 ዓ. ም ቀን ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

የድርጅቱ ባለ ራዕይ እና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ደረጄ ማሙዬ አክለውም ‘’ ድርጅታችን የማህበረሰብ ሃላፊነቱን ለመወጣት የተቸገሩ 54 ያሚሆኑ እናቶችን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመነጋገር 550,000 በለይ በሚሆን አክሲዮን በማበርከት ‘’የጎዶ ሪል ስቴት’’ ባለንብረት ከማድረግ ባለፈ በተለያዩ የማህበረስቡ በዓላት ላይ ድጎማዎችን ሲያደርግ ቆይቷል። ከዚህም በተጨማሪ 24 ለሚሆኑ ወ ጣት ሴቶች የስራ እድልን በመፍጠር የመኖሪያ ቦታ በማዘጋጀት ቀለባቸውን በመቻል እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ስራዎችን በመስራት የማህበረሰብ ሃላፊነቱ እየተወጣ ያለ ድርጅት ነው።

ጎዶ ስማርት ሪል ስቴት

ጎዶ ስማርት ሪል እስቴት የአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ ‹‹1 + 8 > 9 = 150+››  በሚለው ልዩ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ ሲሆን ይህም ራእይ በአንድነት፣ በተደራጀ አስተዳደርና በዘላቂነት ስኬት ላይ የሚያተኩር ከኦሮሞ ጌዳ ሲስተም የተገኘ ጽንሰ ሐሳብ ነው።

ትልቁ የአፍሪካ ኩባንያ ‘’የአፍሪካ ሆልዲንግ ግሩፕ’’ ሼር ካምፓኒ በኢትዮጵያየንግድ ህግ ቁጥር 1243/2013 መሰረት የተቋቋመበት ዋነኛው ግቡ በሀገራችን ብሎም በአፍሪካ ያለውን ተባብሮ የመስራትና ሀብት የመፍጠር ችግሮችን ከመሰረቱ በማጥናትና የመፍቻ መንገዶችን በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን አላማውም በ 2032 አ.ም (ከተቋቋመ ከ10 እመት ውስጥ) ከ20 ሚሊዮን በላይ ባለአክሲዮኖችን በማስተባበር ከ20 ቢሊዮን በላይ ብር በማሰባሰብ ከ150 በላይ ካምፓኒውችን በማቋቋምና ከ155 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ግቡ አድርጎ የተቋቋመ የአፍሪካ ግዙፉ የህዝብ ካምፓኒ ነው። ጎዶ ስማርት ሪል እስቴት፣ ኮዴኮ ካፌ፣ ቡዴና አዮ፣ አጋ አካዳሚ፣ የአፍሪካ የንግድ ማዕከል፣ እና ኦሺን ቴክኖሎጂ የተባሉ የንግድ ዘርፎች ላይ  ተሰማርቶ ይገኛል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe