ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተጠያቂ አደረጉ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትንያሁ ትላንት በአውስትራሊያ አይሁዶች ላይ ለደረሰው ጥቃት የአውስትራሊያውን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተጠያቂ አደረጉ፡፡

ትላንት አውስትራሊያ ሲድኒ 15 አይሁዳዊያን ሲገደሉ ከ40 የማያንሱት ደግሞ የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል፡፡

ቤኒያሚኒን ኔትንያሁ ከአራት ወራት በፊት ለአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ማስጠንቀቂያ ልከው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ አውስትራሊያ በሀገሪቱ ጸረ ሴማዊነት እንቅስቃሴን እያበረታታችና እየደገፈች መሆኑን በመግለጽ ማስጠንቀቂያ ልከው እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ አውስትራሊያ እና ሌሎች ሀገራትም እስራኤል አስከፊውን የጋዛውን ጦርነት እያደረገች ባለበት ወቅት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

በወቅቱም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚንኔትንያሁ የአውስትራሊያ እንዲህ አይነቱ ጥሪ በተቀጣጠለው የጸረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ ላይ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ ነውና ተውት የሚል ደብዳቤ ለአቻቸው ጽፈውላቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ቤኒያሚንኔትንያሁ እሁድ እለት በአውስትራሊያ አይሁዶች የደረሰውን አስከፊ ጥቃት አውግዘው ለጠቅላይሚኒስትር አልባኔዝም ማስጠንቀቂያ ሰጥተው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይሚኒስትር አልባኔዝ ግን የኔትንያሁን ክስ አይቀበሉትም፡፡ በተጨማሪም መንግስታቸው የጸረ ሴማዊነት እንቅስቃሴን እንደማይቀበለው በመግለጽ፡፡

በአውስትራሊያ እሁድ እለት የአይሁድ በዓልን በማክበር ላይ የነበሩ 15 አይሁዳዊያን በሲዲኒ የባህር ዳርቻ ተገድለዋል፡፡ ኔትንያሁ ይህንን አስደንጋጭ ክስተት አውግዘው ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠት በጸረ ሴማዊነት ላይ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ የሚቆጠር ተግባር በማለት ከሰዋል፡፡

ትላንት በሲዲኒ አይሁዶች ላይ ጥቃት ያደረሱት ደመ ቀዝቃዛ አጥፊዎች ናቸው ሲሉ ኔትንያሁ ተናግረዋል፡፡ ከገዳዮቹ አንዱ እንደሆነ የተጠረጠረው የ50 ዓመቱ ጎልማሳ እንደተገደለ ሲሰማ፤የ24 ዓመት ወጣት የሆነው ልጁ ደግሞ ቆስሎ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ አክለውም በነሃሴ ወር ለጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ  የአውስትራሊያ መንግስት ጸረ ሰማዊነትን በሀገሪቱ እየደገፈ እንደሚገኝ የሚገልጽ ደባብዳቤ በመላክ አስጠንቅቄ ነበር ብለዋል፡፡ የአውስትራሊያ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠትም በጸረ ሴማዊነት እሳት ላይ ተጨማሪ ነዳጅ እንደመጨር መሆኑንና ድርጊቱም ሽብርን እንደመሸለም የሚቆጠር እንደሆነ ተናግሬ ነበረ ብለዋል፡፡

በነሃሴ ወር የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አልባኔዝ አውስትራላያ በመስከረም በሚደረገው የተመድ የጽታው ም/ቤት ስብሰባ ላይ ፈረንሳይን፡እንግሊዝን እና ካናዳን ተከትላ ለፍልስጤም እውቅና እንደምትሰጥ ተናግረው ነበር፡፡

አልባኔዝ በአውስትራሊያ ጸረ ሴማዊነትን ለማስቆም ምንም እንዳልሰሩ በማንሳት ከሰዋል፡፡ እንዲያውም ይህ የጸረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ እንዲስፋፋ ተደርጓል፤ውጤቱንም ዛሬ ይህንን አሳዛኝ ዜና በመስማት አይተነዋል ብለዋል፡፡

ይህ አስደንጋጩ ክስተት የተፈጠረው አይሁዳዊያን ሃኑካህ የተሰኘውን በዓላቸውን በቦንዲ የባህር ዳርቻ እያከበሩ ባለበት ወቅት ነው፡፡//

እስራኤል በጋዛ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለማደናቀፍ ሲሰራ ነበር ያለችውን የሃማስን መሪ ገደለች፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሃይል ራድሳድ የተባለውን የሃማስን መሪ መግደሉን ይፋ አድርጓል፡፡ ይሔው ግለሰብ ሃማስ አቅሙን ዳግም እንዲያደራጅ ሲጥር የነበረ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

የእስራኤል ጦር ነባር የቡድኑ ኮማንደር የሆነውን ራድሳድ ቅዳሜ እለት ነው ያስወገደው፡፡ ኮማንደር ራድሳድ በአሜሪካ አደራዳሪነት የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሚፈለገው መጠን እንዳይተገበር እንቅፋት ሆኖ የቆየ መሆኑንም ጦሩ አስታውቋል፡፡

ኮማንደሩ የቡድኑ ወታደራዊ ክንፍ መሪ ነበር ተብሏል፡፡ የኮማንደሩ ግድያ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ካለፉት ወራ ወዲህ የተደረገ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ግድያ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

ሃማስ የእስራኤል የውጊያ አውሮፕላኖች የንጹሃን ተሸከርካሪዎችን በምዕራብ ጋዛ አካባቢ ኢላማ ማድረጋቸውን የገለጸ ሲሆን ጉዳቱን በተመለከተ ግን ይፋ ያደረገው መረጃ አልተሰማም፡፡

ትላንት እሁድ የቡድኑ ዋነኛ ተደራዳሪ እንደሆነ የሚታመነው እና በአንድ ወቅትም በኳታር ዶሃ ከእስራኤል የአየር ጥቃት የተረፈው ካህሊል አልሃያ ራድሳድ እና ሌሎች በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ተናግሯል፡፡

ኮማንደር ራድሳድ የኦክቶበር 7ቱን እልቂት በማቀድ ውስጥ ተሳታፊ ነበር የተባለ ሲሆን፤አሁንም ከስምምነቱ ውጪ የቡድኑን አቅም ለመገንባት በጥረት ላይ የቆየ እንደነበረ ነው የእስራኤል ጦር የገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደም በ2024 የእስራኤል ጦር ሳድን ኢላማ አድርጎት እንደነበርም ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡ ይህ ዜና የተሰማው እስራኤል እና ሃማስ ወደ ሁለተኛው እና ወሳኙ ምዕራፍ ሊገቡ ነው ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ወቅት ነው፡፡ በዚህኛው ምዕራፍ የሃማስን ትጥቅ መፍታትን እንዲሁም የእስራኤል ወታደሮች ከያዙት ስፍራ ለቀው መውጣትን ጨምሮ ሌሎች ውስብስብ ጉዳዮች ይፈጸሙበታል ተብሎ የሚጠበቅበት ነው፡፡

ነገር ግን አሁንም ቢሆን ግን የአንደኛው ምዕራፍ ሙሉ በሙሉ ገና አልተጠናቀቀም፡፡ ሃማስ አንድ የእስራኤልን አስክሬን ገና አላስረከበም፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe