ኢራን ጦርነቱን ለመቋጨት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ብቻችወን እያወሩ ነው” አለች

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሀገራቸው ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለመቋጨት የሚያስችል “በጎ እና ውጤታማ” ውይይት ማድረጓን ቢያስታውቁም ኢራን ኝ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ<ብቻችወን እያወሩ ነው> አለች።
​ፕሬዝዳንት ትራምፕ በራሳቸው የማኅበራዊ ትስስር ገጽ (Truth Social) ባሰፈሩት መረጃ ላለፉት ሁለት ቀናት ከኢራን ጋር የተደረገው ንግግር ውጥረቱን ሙሉ በሙሉ ሊያስቀር የሚችል መሆኑን ገልጸዋል።
​ይህ እርምጃ ለሳምንታት የዘለቀውንና ዓለም አቀፍ ስጋት የፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት ትልቅ ተስፋ ሰጥቷል።
​ውይይቱን ስኬታማ ለማድረግና ለሰላም ዕድል ለመስጠት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሚከተለውን ወሳኝ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
​የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) በሚቀጥሉት አምስት ቀናት ውስጥ በኢራን የኃይል እና የኢነርጂ መሰረተ ልማቶች ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት እንዳይሰነዝር ታዝዟል።
​ይህ አዲስ የሰላም ተስፋ የመጣው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቀደም ሲል የሰጡትን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ነው።
​ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቴህራን ላይ በኢራን የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም አስቀምጠውት የነበረውን የ48 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ወደ አምስት ቀን አራዝመዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛው ምሥራቅ ስላለው ግጭት ከኢራን ጋር “ሙሉ በሙሉ እና አጠቃላይ መፍትሔ” መድረስን በተመለከተ “ውጤታማ ውይይቶች” ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “በኢራን የኃይል ማመንጫዎች እና የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን ሁሉ ለሌላ ጊዜ አስተላልፋለሁ” ብለዋል።
ትራምፕ ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን በ48 ሰዓትት ውስጥ ካልከፈተች የኃይል ማመንጫዎቿን ለማጥቃት ዝተው የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ለመጪዎቹ አምስት ቀናት እርምጃውን ማዘግየታቸውን ገልጸዋል።

ዋሽንግተን እና ቴህራን በጉዳዩ ላይ ሳምንቱን ሙሉ ንግግራቸውን እንደሚቀጥሉ ቢናገሩም  ኢራን ግን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተደረገ ንግግርም ሆነ ውይይት የለም <ብቻችወን እያወሩ ነው> በላለች፡፡

የኢራን መንግሥት በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኩል የቀረበውን የድርድር ዕቅድን ውድቅ ማድረጉን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን አመለከቱ።

የኢራን መንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያ የሆነው ፕሬስ ቲቪ የአገሪቱን “ከፍተኛ የፖለቲካ እና የደኅንነት ባለሥልጣናትን” ጠቅሶ እንደዘገበው፤ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም በማለም በአሜሪካ በኩል የቀረበውን ሃሳብ ኢራን ውድቅ አድርጋዋለች።

የቴሌቪዥን ጣቢያው የባለሥልጣኑን ስም እና የሥራ ኃላፊነት ሳይጠቅስ እንደዘገበው “ኢራን ጦርነቱን የምታበቃው ራሷ ስትወስን እና የራሷ ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው” ሲሉ ባለሥልጣኑ መናገራቸውን አመልክቷል።

የኢራን ባለሥልጣናት እስካሁን ድርድር አለመጀመሩን እንዲሁም ጦርነቱ የሚቆም ከሆነ የተኩስ አቁም ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ መሆን እንዳላበት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።

የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ፕሬስ ቲቪ እንዳመለከተው፣ ባለሥልጣኑ ኢራን መሟላት አለበት ያለቻቸውን የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ገልጸዋል።

በጠላት የሚፈጸመው “ወረራ እና ግድያ” ሙሉ ለሙሉ መቆም
ጦርነቱ በድጋሚ በኢራን ላይ እንደማይከፈት የሚያረጋግጥ አስተማማኝ ሁኔታ መፍጠር
የተረጋገጠ እና በግልጽ የሚታወቅ በጦርነቱ ለደረሰው ጉዳት እና ካሳ መክፈል
በቀጣናው ባሉ ቡድኖች ላይ የተከፈቱት ሁሉም ጦርነቶች እንዲቆሙ ማድረግ
ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያላትን መብት እና ሉዓላዊነት ዓለም አቀፍ ዕውቅና መስጠት የሚሉ ናቸው።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን በኩል ከቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች በአብዛኛው ተቃራኒ የሆኑ ባለ 15 ነጥብ የድርድር ዕቅድ ማቅረባቸው የተነገረ ሲሆን፣ የኢራን ባለሥልጣናት ግን ነጥቦቹ “ከልክ ያለፉ ናቸው” በማለት መቃወማቸውን ፕሬስ ቲቪ ዘግቧል።

/
​

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe