ፀሐይ ባንክ አ.ማ. በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት በወሳኝ የአፈፃፀም መለኪያዎች የተሻለና አበረታች ውጤት አስመዝገበ

ፀሐይ ባንክ አ.ማ. በተጠናቀቀው 2025/26 ሒሳብ ዓመት በወሳኝ የአፈፃፀም መለኪያዎች የተሻለና አበረታች ውጤት አስመዝገበ፡፡
ፀሐይ ባንክ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2026/27 ሒሳብ ዓመት ዕቅድ የውይይት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ሆቴል ትናንት ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም አካሒዷል፡፡
ባንኩ በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት በወሳኝ መለኪያዎች የተሻለና አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገልጿል፡፡
በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን የገለጹት የፀሐይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ መስፍን፤ በተያዘው አዲስ በጀት ዓመት የበለጠ ስኬትን ለማስመዝገብ መላው የባንኩ ማኔጅመንት እና ሠራተኞች በትጋትና በመናበብ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሠራተኞቹም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡
በመጨረሻም በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች የእውቅና አሰጣጥ መርሐግብር ተከናውናል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe