አውሮፓዊቷ ሀገር ፈረንሳይ በአምስት ቀናት ብቻ በሙቀት ምክንያት 1000 ሰዎች ሞተዋል የተባለ ሲሆን፤ከሟቾቹ ውስጥም ከ85 በመቶ በላይ የሚሆት እድሚያቸው ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸው እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
ሁኔታውን ተከትሎም በፓሪስ በርካታ ዝግጅቶች ተሰርዘዋል፤ጥቂት ፖለቲከኞችም መንግስት አስቀድሞ ዝግጅት ማድረግ ስላልቻለ አሁን የተፈጠረው ነገር ሆኗል በማለት የማክሮንን አስተዳደር ተችተዋል፡፡
በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ያለው የሙቀት መጠን ከ40 ዲግሪሴንቲግሬድ መብለጡንም ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡ የደረንሳይ የጤና ባለስልጣናት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ብቻ በዚሁ ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺ በልጧል ብለዋል፡፡
አሁን በፈረንሳይ እየታየ ያለው ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ የተመዘገበው እጅግ የከፋው የሙቀት መጠን ነው ተብሏል፡፡
በዚህ ስዓት አብዛኛው የፈረንሳይ ክፍል ከ40 ዲግሪሴንቲግሬድ በላይ ነው የተባለ ሲሆን፤ማክሰኞ እለት ደግሞ በመላው ሀገሪቱ ከ2003 ወዲህ እጅግ ከፍተኛው ሞቃታማ ቀን ሆኖ አልፏል ሲል RT ጽፏል፡፡
ከፈረንሳይ በተጨማሪ በጀርመን እና ቼክ ሪፐብሊክም ትላንት እሁድ ከ41 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ተመዝግቧል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአውሮፓ የስራ ቦታዎች እና ትምህርት ቤቶች አሁን ለተፈጠረው የአየር ጸባይ ተስማሚ ሆነው መገንባት እንደሚገባቸው ማሳሰቢያ በኤክስ ገጻቸው ጽፈዋል፡፡

