ፍርድቤቱ ሼኽ መሐመድ አልአሙዲን 852 ሚሊዮን እንዲከፈላቸዉ አዘዘ

ሼኽ መሐመድ አልአሙዲን፣ አቶ አብነት ገ/መስቀል ለብልጽግና ፓርቲ “ሰጥተውብኛል” ያሉትን 75 ሚሊየን ብር ጨምሮ፣ ለተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ከዚህ ቀደም በስጦታ መልክ የተለገሰውን ገንዘብ አቶ አብነት “ይመልስልኝ” ሲሉ ፍርድ ቤት ክስ መስርተው ሲከራከሩ ነበር፡፡

የክስ መዝገብ እንደሚለውም፣ የናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኩባንያ ከ2004 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ ካተረፈው ትርፍ ላይ፣ ለአልአሙዲ ይደርሳቸዋል ተብሎ በኩባንያው ከተረጋገጠው አጠቃላይ የትርፍ ድርሻ ውስጥ፣ በአቶ አብነት የባንክ ሂሳብ 852 ሚሊዮን 462ሺ 650 ብር ገቢ ተደርጓል።

ሰነዱ እንደሚገልጠው፣ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ፣ ከ581 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግሥት ተቋማትን ጨምሮ ለመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በሼኽ አልአሙዲ ፍቃደኝነት ከአቶ አብነት የባንክ ሂሳብ ተከፍሏል። ከዚህ የብር መጠን ውስጥም፣ ለብልጽግና ፓርቲ 75 ሚሊዮን  ብር መከፈሉን የሚጠቅሰው ይህ የፍርድ ቤት ሰነድ፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሶሻል ትረስት ፈንድ 120 ሚሊዮን ብር፣ ለፌደራል ፖሊስ 5 ሚሊዮን ብር እና ለኢንፎርሜሽን ደኅንነት መረብ ኤጀንሲ 7 ሚሊዮን ብር መሰጠቱን ያትታል።

እነዚህ እና ሌሎች በሰነዱ የተጠቀሱትን ክፍያዎች አስመልክቶም፣ ሼኽ ዓሊ አልአሙዲ፣ አቶ አብነትን የወከልኩት ስጦታ እንዲሰጥልኝ አይደለም ሲሉ፣ እነዚህን ክፍያዎች ይመልስልኝ ሲሉ ተሟግተዋል። የፍርድ ቤቱ የከሳሽ እና የተከሳሽ ሰነዶች እንደጠቆሙት፣ ተከሳሹ አቶ አብነት ገ/መስቀል፣ እነዚህን ክፍያዎች ወጪ ያደርኩት በተሰጠኝ ውክልና በመሆኑ፣ ያደረኩት የውክልና ግዴታዪን መፈፀም ብቻ በመሆኑ ልከሰስ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል።

ክሱን ሲመለከት የነበረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም፣ አቶ አብነት ለብልፅግና ፓርቲ የተከፈለውን 75 ሚሊዮን ብር ጨምሮ፣ በክሱ የተዘረዘሩትን ክፍያዎች ሲከፍሉ ለአልአሙዲ ጥቅም ያልተፈጸሙ በመሆናቸው፣ ተከሳሹ አቶ አብነት ገ/መስቀል የተከሰሱበትን 852,462,650 ብር ለአልአሙዲ እንዲከፍሉ ሲያዝ፣ የይግባኝ መብት እንዳላቸው ጠቅሶ ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe