ፕሬዜዳንት ረሲፕ ኤርዶዋን ዋነኛ ተፉካካሪያቸውን ማሰራቸው መዘዝ ይዞባቸው መጣ

የቱርኩ ፕሬዜዳንት ዋነኛ ተፉካካሪያቸውን ማሰራቸው መዘዝ ይዞባቸው መጥቷል፡፡ የተነሳባቸውም ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል ተብሏል፡፡

የፕሬዜዳንት ረሲፕ ኤርዶዋን ቀንደኛ ተቀናቃኝ በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ተከትሎ በመላው ቱርክ የተነሳው ከፍተኛ ተቃውሞ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

ኤክሬም ኢማሞግሉ የኢስታንቡል ከንቲባ ሲሆኑ ከሦስት ዓመታት በኋላ ለሚካሄደው ምርጫ የሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ ዕጩ ሆነው ትላንት ይመረጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር፡፡

ሰውየው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ቱርክ ላለፉት 10 ዓመታት አይታ በማይታወቀው ተቃውሞ እየተናጠች ነው ተብሏል፡፡ ፖሊሶችም አመጹን ለማርገብ አስለቃሽ ጭስ እና የጎማ ጥይት በመተኮስ ላይ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

ኢማሞግሉ እሳቸው ላይ የተከፈቱ ክሶች ፖለቲካዊ መሆናቸውን በመግለጽ በፍጹም አላጉበድድም ሲሉ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈው ነበር ተብሏል፡፡

ፕሬዜዳንት ኤርዶዋን ደግሞ ሰልፈኞቹን ወቅሰው ፓርቲው ሰላማችንን ሊበጠብጥ እና ህዝባችንን ሊከፋፍል የተነሳ ነው በማለት ወቅሰዋል፡፡

ከንቲባው በይፋ በቁጥጥር ስር የዋሉት ትላንት እሁድ ነው፡፡ ወንጀለኛ ቡድን በማቋቋም እና በማስተዳደር፡ሙስና በመቀበል እና ግላዊ መረጃ በመቅዳት እንዲሁም ጨረታ በማጭበርበር ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡//
 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe